አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4/2014 ዓ.ም፡– የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተባበሩት መንግስታት ለኢትዮጵያ የተሾሙት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን ጳጉሜ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ማዘኑን ገልጾ በፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ የማቅረብ ስልጣን የላቸውም ሲል ጥሪውን ውድቅ አደረገ።
የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ከትናንት በስቲያ የኢትዮጵያ መንግስትን ለጦርነቱ ተጠያቂ በማድረግ የተመድ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቦ ነበር።
ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴሯ በኩል ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ኮሚሽኑን “ለፖለቲካዊ ጫና የሰብአዊ መብትን የጦር ማሳሪያ አድረጓል” ስትል ከሳለች፡፡ በማከልም የሰሞኑ መግለጫው “እውነተኛ አላማውን ያጋለጠና ከመንግስት ጋር ያለውን የትብብር በሮች የዘጋ ነው” ስትል ተናግራለች።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው “ኮሚሽኑ ህወሓት ሰብአዊ እርቅን በመጣስ ላስነሳው ግጭት ምንም አይነት ግንዛቤ የለውም። ኮሚሽኑ ለሰላምና ለደህንነት ጠንቅ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለራሱ ስልጣን ሊሰጥ አይችልም” ሲል ገልጾ የኮሚሽኑን ጥሪ “በፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ የማቅረብ ስልጣን የላቸውም ሲል አክሏል፡፡
ሚኒስቴሩ አክሎም ኮሚሽኑን “ኃላፊነት የጎደለው ባህሪ” ማሳየቱን እና መንግስት የኮሚሽኑ እንቅስቃሴና ስራ ፖለቲካዊ ይዘት አለው በሚል የሚያነሳውን ሃሳብ ያረጋገጠ ሆኗል ምነው ያለው።
ሚኒስቴሩ በማጠቃለያው በኮሚሽኑ የተሰጠውን መግለጫ ውድቅ ካደረገ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የሰበአዊ መብቶችን በማስከበር አጥፊዎችን ለህግ በማቅረብ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡
በፌደራል ሰራዊት እና በትግራይ ሃይሎች መካከል ለሁለተኛ ጊዜ ስለጀመረው ወታደራዊ ጦርነት አስተያየት የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አባላት ከሁኔታው አሳሳቢነት አንጻር ምክር ቤቱ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይን በአጀንዳው ላይ እንዲያኖር አሳስቧል።
ኮሚሽኑ አክሎም “የኤርትራ ወታደሮችም ጦርነትን ውስጥ መሳተፋቸውን ገልጦ ግጭቱ ወደ ሌሎች ክልሎች የመዛመት አደጋ አለው” ሲል አስጠንቅቋል።
ኮሚሽኑ በድጋሚ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሃት መካከል ያገረሸው ግጭት እንዳሳሰበው ጠቅሶ ሁሉም ወገኖች ጦርነቱን እንዲያቆሙ፣ በአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋት የተጣለባቸውን ግዴታ እንዲያከብሩ እና ሁሉም አካላት በአስቸኳይ ወደ ውይይት መድረክ እንዲመለሱ ጥሪው ማቅረቡ ይታወሳል።አስ