አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2015 ዓ.ም፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ ለደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ኢትዮጵያ ባላት አቅም የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ ማበርከቷን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት በቱርክ ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
“በቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ በጠፋው የሰው ሕይወት እና በወደመው ንብረት የተሰማኝን ጥልቅ ኀዘን ለፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ገልጫለሁ” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የተቸገረ ወዳጇን ለመርዳት ምንጊዜም ቁርጠኛ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባላት አቅም የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ ማበርከቷንም ጨምረው ገልፀዋል።
በቱርክ እና ሶሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 45, 000 ማለፉ ተገልጿል።
ከነዚህም ውስጥ በቱርክ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 39, 672 ደርሷል። የሶሪያ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገጹት ደግሞ በሶሪያ ከ5, 800 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል። አስ