አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1/2015 ዓ.ም፡- የኬንያ ባለሃብቶች መዋእለነዋያቸውን ለማፍሰስ በይበልጥ ይመርጧቸው የነበሩ ሀገራት ታንዛንያ እና ኡጋንዳ እንደነበሩ ይገለጻል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ኬንያውያኑ ተመራጭ እያደረጓት ያሉት ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን የሀገሪቱ ትልቁ የሚዲያ ተቋም ኔሽን በድረገጹ አስነብቧል።
እንደ ኔኝን ዘገባ ከሆነ በ2021 የኬንያውያን ባለሃብቶች ከ60 ቢሊየን የኬንያ ሺሊንግ በላይ ሀብታቸውን በኢትዮጵያ አፍስሰዋል። ለበርካታ አመታት የኬንያ ባለሃብቶችን ቀልብ ሲስቡ የነበሩት ኡጋንዳ እና ታንዛንያ ደግሞ 56 ቢሊየን ሺሊንግ እና 51 ቢሊየን ሺሊንግ የኬንያውያንን ሀብት በመሳብ ኢትዮጵያን በመከተል ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን መያዛቸውን ዘገባው አስታውቋል።
ታንዛንያ ከ2015 ጀምሮ ለተከታታይ አመታት አንደኛ ተመራጭ የኬንያውያን ባለሃብቶች መዳረሻ እንደነበረች ያወሳው ዘገባው ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ኡጋንዳ እና አዲስ አበባ ቦታዋን እንደወሰዱባት አመላክቷል።
በቅርቡ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍን የተቀላቀለው ሳፋሪኮም በአስር አመታት ውስጥ የሀገሪቱን 40 በመቶ ገበያ ለመቆጣጠር አቅዶ እየሰራ መሆኑን ጋዜጣው ጠቁሟል። ከወራት በፊት የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የኬንያው ትልቁ ባንክ ኬሲቢ በኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ለመሰማራት ልዑካንን በመላክ እና ጥናት በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አመላክቷል። አስ