ዜና፡ አሜሪካ “የኤርትራን ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ግጭት” መግባት አወገዘች፤ የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛዋን በመላክም ሁሉም ወገኖች ወደ ሰላማዊ የድርድር መድረክ እንዲመጡ አሳስባለች

የኤርትራ ጦር በትግራይ ጦርነት ውስጥ መሳተፉን ከሚያሳዩት የመጀመሪያ ሥዕሎች አንዱ በሮይተርስ ጋዜጠኛ ዳዊት እንደሻው በመጋቢት2014። ክሬዲት፡ ዳዊት እንደሻው

በአዲስ ስታንዳርድ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም፡- አሜሪካ ነሐሴ 18 እንደአዲስ በፌደራል መንግስቱ ሰራዊት እና በትግራይ ሀይሎች ያገረሸውንና እስከ ሱዳን ድንበር ድረስ የተስፋፋውን ጦርነት ተከትሎ “የኤርትራን ዳግም ወደ ጦርነቱ መቀላቀል” በጥብቅ እንደምታወግዝ አስታውቃለች።

ነሐሴ 27 ቀን ፕሬስ ሴክሬታሪያት ካሪን ጂን ፒየር በዋይትሐውስ በሰጡት መግለጫ ላይ ” የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ቀውስ በተመለከተ ለመነጋገር ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ” ብለዋል አያይዘውም “ልዩ መልዕክተኛው ሁሉም አካላት ማናቸውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያቆሙና ወደ ሰላማዊ የድርድር መድረክ እንዲመጡ የመንግስታቸውን መልዕክት ያስተላልፋሉ ” ሲሉ ገልፀዋል

አሜሪካ የኤርትራ እንደገና ወደ ግጭት መግባቷን ከማውገዝ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል ውጭ የቀጠለውን የህወሃት ጥቃት እና የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ድብደባ አውግዛለች።

“ለግጭቱ ምንም ዓይነት ወታደራዊ መፍትሔ የለም። እንደ አዲስ ካገረሸው ጦርነት አስቀድሞ ለአምስት ወራት ያክል በቆየው የሰብዓነት ዕርቅ ተበረታተን የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን በጦርነቱ ምክንያት ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ አለመቻላችን በእጅጉ አሳስቦናል ” ሲሉ የአሜሪካው ፕሬስ ሴክሬታሪያት ካሪን ጄን ፒየር ተናግረዋል፡፡ አክለውም ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ጦርነቱን አቁመው ወደሰላማዊ የመፍትሔ አማራጮች እንዲመጡና የሰብዓዊ እርዳታዎችንና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማስቀጠል እንዲቻል አጥብቀው ጠይቀዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት የኤርትራን በጦርነቱ ውስጥ መሳተፏን በመቃወም የሰነዘረችው ውግዘት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ባሁኑ ጦርነት   ውስጥ  ዳግም የመሳተፏ የመጀመሪያው ማረጋገጫ ነው።

የኤርትራ ወታደሮች በትግራዩ ጦርነት ላይ ስለነበራቸው ሚና እና በንፁሃን ዜጎች ላይ ተፈፅመዋል ስለተባሉ አሰቃቂ ድርጊቶችን በተመለከተ የተለያዩ አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚደገፈው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመጉ) ጨምሮ ያወጧቸውን ሪፖርቶች የኢትዮጵያ መንግስት “ፍፁም ውሸት ” ሲል ካስተባበለ በኋላ በወርሃ ግንቦት 2021 ላይ “በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት” ስለመኖሩ ማረጋገጫ መስጠቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የኤርትራን ዳግም ወደ ተቀጣጠለው ወታደራዊ ጦርነት መግባት እያስተባበለች ነው። በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ትላንት ነሐሴ 27 ቀን  ለሲኤንኤን  “በፍፁም በጉዳዩ ላይ መረጃ የለንም፤ የምንሰማው  በማህበራዊ ሚዲያ ነው …” ብለዋል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም “ህወሃት ኤርትራ ወደ ግጭት እንድትገባ የመሳብ ባህሪ አለው…” በማለት ህወሃትን ከሰዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.