ዜና፡ አሜሪካ ኦሮሚያ ውስጥ ያለውን አለመረጋጋት ወደ መቋጨት ትኩረቷን አዞረች፤ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ መውጣት መጀመራቸውን አረጋገጠች

አዲስ አበባ፣ ጥር 15/2015 ዓ.ም፡- የአሜሪካ መንግስት ትኩረቱን ኦሮሚያ ክልል ወዳለ ግጭት በማዞር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን ግጭት መቋጨት እንደሚያስፈልግ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ገለፁ፡፡

ይህ የተባለው በፌዴራል መንግስትና መንግስት “ሸኔ” ብሎ በሚጠራው በታጠቁ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት መካከል የተኩስ ልውውጦች እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው፡፡ ታህሳስ 25 ቀን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በደቡብ ኦሮሚያ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን አማፂ ቡድን ለማጥፋት እና ክልሉን ለማረጋጋት ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን እና ኦፕሬሽኑ ” መሳካቱን ” እንዲሁም ሰራዊቱ “በደቡብ ኦሮሚያ የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን ማስለቀቅ መቻሉን  ገልፆ ነበር፡፡

በዝያኑ ሳምንት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት በምእራብ ጉጂ ቡሌ ሆራ ውስጥ እስር ቤት ሰብረው በመግባት ከ480 በላይ የሚሆኑ እስረኞጭ ማስለቀቃቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግባለች፡፡

ከአራት አመታት በፊት የተጀመረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በርካታ ጥሪዎች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ህዳር 26 የመሪው ብልፅግና ፓርቲ አባላት የሆኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  አባላት በኦሮሚያ ሰላም ለማስፈን አስር ነጥቦችን ያካተተ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚንስትሪ እና ለፓርላማ አፈ ጉባኤ አስገብተዋል፡፡ የምክር ቤት አባላቱ መንግስት ከህወሃት ጋር ያሰደረገውን የሰላም ስምምነት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋርም እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ሲል አንድ የምክር ቤት አባል ገልጧል፡፡

የአሜሪካ መንግስት ያወጣው መግለጫ ስለ ውይይቱ ዝርዝር መረጃም ሆነ አለመረጋጋትን ለማስቆም ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ምንም መረጃ ባይሰጥም፤ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በፖለቲከኞች አድናቆት የተቸረው ሲሆን ጀዋር “ የአሜሪካ መንግስት በኦሮሚያ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ግፊት ማድረግ መጀመሯን በማየቴ ድስ ብሎኛል” ሲል በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።

በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ እና የአማራ ሀይሎችን በተመለከተ ብሊንከን በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ወታደሮች እየወጡ ነው ብለዋል፡፡ ይህም በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አርብ እለት የኤርትራ ወታደሮች ከአክሱምና አዳዋ አካባቢዎች ለቀው እየወጡ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ “ከሁለት ቀን በፊት ወደ አዲ በራኽ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑ መኪኖች አልፈዋል። የዛሬውን ለየት የሚያደርገው አንዱ ነገር ብዛት ያለው ሠራዊት መሆኑ እና ሁሉንም ነገር የጫኑ መሆናቸው ነው። ፀረ አውሮፕላን የጫኑ ተሸከርካሪዎች ሳይቀሩ አልፈዋል።” ሲሉ አንድ የአደዋ ከተማ  ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ይህ መረጃ የትግራይ ሃይሎች ትጥቅ መፍታታቸውን በገለፁት በአፍሪካ ህብረት የተሸሙት በሰላም ስምምነቱ ተቆጣጣሪዎች አልተረረጋገጠም፡፡

ህዳር 3 ቀን በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት በፕሪቶርያ የተደረሰው ስምምነት መሰረት “የትግራይ ሃይሎች ትጥቅ የማስፈታት ተግባር ተፈጻሚ የሚያደርገው በአንቀጽ 2.1/D ስር “የከባድ መሳርያ ትጥቅ ማስረከብ የውጭ ሃይሎችና ከኢትዮጵያ መከላክያ ውጭ የሆኑት ታጣቂዎች ከክልሉ ሲወጡ እንደሆነ” ተገልጿል።

ብሊንከን ለአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆጣጣሪዎች እንዲገቡ የጠየቁ ሲሆን ለጠ/ሚ አብይ አህመድ “አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት” ገልፀዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.