አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28/2015 ዓ.ም፡– ከመቶ አመት በላይ በአሜሪካ የውጭ ግንኙነት ዙሪያ ጥናት በማቅረብ ከፍተኛ ተጽእኖ በማሳደር ይታወቃል፤ ካውንስል ኦን ፎሬን ሪሌሽን። መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው ካውንስል ኦን ፎሬን ሪሌሽን በቅርቡ ‘‘Ethiopia’s Mixed Signals’’ በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቃው ጽሁፍ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ያልጠራ፣ የተወሳሰበ እና ስስ ነው ሲል ገልጾታል።
ኢትዮጵያ በአንድ ግዜ ወደ ሁለት አቅጣጫ እየተጓዘች ትገኛለች ሲል የገለጸው ቲንክ ታንኩ አሜሪካ ሚዛናዊ ሚናዋን ለመጫወት እንደተቸገረች አመላክቷል። አወንታዊ እድገቶች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ያስታወቀው ካውንስሉ ነገር ግን የኢትዮጵያ ችግር አይቶ እንዳላየ መሆን መፍትሔ አይሆንም ሲል አሳስቧል።
ዋሽንግተን በጠንቃቄ ነገሮችን እንድትመዝን የመከረው ተቋሙ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ መደበኛ ሁኔታ እየተመለሰ ለመሆኑ ሁነኛ ምልክቶችን እንድትፈልግ አሳስቧል። ውሳኔ ሰጪ አካላት በመጥፎ ተጽእኖ ፈጣሪዎች አስገዳጅ ሁኔታ ላይ አለመውደቃቸውን፣ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች መከበራቸውን እና የመሪዎች ቁርጠኝነት መለካት ያለበት መሬት ላይ ባሉ ልማት እና እድገቶች መሆን እናደለባቸውም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ያለውን ግንኙነት ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር ያካሄደውን የሰላም ውይይት በአወንታዊነት የጠቀሰው ተቋሙ በርካታ በሀገሪቱ የሚታዩ ጠቋሚ ምልክቶች ግን ውስብስብነትን እና አደጋን የሚያሳዩ ናቸው ብሏል።
የሱዳን መመሰቃቀል በቀጠናው ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የለውጥ ሂደት በብርሃን የተላበሰ እንዲመስል አድርጎታል ሲል የገለጸው ቲንክ ታንኩ በሀገሪቱ አሁንም ያልተፈቱ ያላቸውን ችግሮችን በመዘርዘር ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲል መክሯል።
አለም በቅርቡ ኢትዮጵያ እየተንኮታኮተች ነው የሚል ስዕል ይዞ እንደነበር ያወሳው ካውንስል ኦን ፎሬን ሪሌሽን አሁን ግን የበለጸገች እና ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ ለቀጠናው ብሎም ለአህጉሩ አስፈላጊ መሆኗን መገንዘቡን አስታውቋል። ነገር ግን አሁንም ያልተገለጡ እና አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጿል።
በትግራይ ያለውን አሁናዊ ሁኔታ በማሳያነት የጠቀሰው ቲንክ ታንኩ ጦርነቱ ቢያበቃም የህዝቡ መከራ መቀጠሉን፣ አሁንም አወዛጋቢ በሆኑ የክልሉ ድንበሮች መፈናቀል መቀጠሉን፣ የኤርትራ ጦር እና የአማራ ሚሊሻዎች ከትግራይ ለቀው አለመውጣታቸው፣ የረድኤት ድርጅቶች እርዳታ ማከፋፈል ማቆማቸውን በዝርዝር አስነብቧል።
ባለፈው ሳምንት የአማራ ክልል ከፍተኛባለስልጣን ግርማ የሺጥላ መገደል አሁንም በኢትዮጵያ ስጋት በመንተግተግ ላይ መሆኑን ማሳያ ነው ሲል ገልጿል። አስ