አዲስ አበባ፣ ጥር፣ 2/2015 ዓ.ም፡- የ65 አመቱ ተከሳሽ ሀምሳ አለቃ ጀምበር ታከለ በጎንደር ዙርያ ወረዳ ላየ ዱጌ ቀበሌ ከባድ በሆነ ጭካኔ እና ግፍ በተሞላበት አምስት ሰዎችን በመግደል እና አምስት ሰዎችን ደግሞ የመግደል ሙከራ ወንጀል በመፈፀሙ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ፡፡
ግለሰቡ ጎንደር ዙርያ ወረዳ ዱጌ አብርሐም ቀበሌ ነዋሪ የሆነ ሰው ለመግደል አስቀድሞ በማሰብ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 3:00 ሰአት ሲሆን በወረዳው ላየ ዱጌ ቀበሌ ልዩ ቦታው ዱጌ አብርሐም ቤተክርስቲያን፣ ለለቅሶ በቤተክርስቲያን ከተሰበሰበበት ሁለት እግር ታጣፊ ክላሽ የንምራ ቁጥር የለለው ጠመንጃ ይዞ በመምጣት አምስት ሰዎችን ገድሏል፡፡
ተከሳሹ 1ኛ/ ማች አቶ አብዩ ቢያዝን 2ኛ/ ማች አቶ ግስሜ ጌታነህ በያዘው ክላሽ ጠመንጃ ሁለት ጥይት ተኩሶ መትቶ ከገደላቸው በኋላ ለልቅሶ ከተሰባሰበው ሕዝብ የያዘውን ቦንብ በመወርወር 3ኛ/ ማች አቶ ወሌ ዳኘው 4ኛ/ ማች አቶ ሰማቸው አጥናፉ 5ኛ/ ማች አቶ ፈንቴ ደምሴ ተወርወሮ በወደቀው ቦንብ ተመትተው ወዲያውኑ ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል፡፡
በተጨማሪም 6ኛ/ የግል ተበዳይ አቶ ክፈተው ጌታነህ 7ኛ/ የግል ተበዳይ አቶ ፍቃድ ግዛልኝ 8ኛ/ የግል ተበዳይ አቶ ጎዳዳው ይርዳው 9ኛ/ የግል ተበዳይ አቶ ተስፋየ ዳኘው 10ኛ/ የግል ተበዳይ አቶ መኩሪያው ፀሀይ ላይ ተወርውሮ በፈነዳው ቦንብ ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
የጎንደር ዙርያ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት የምርመራ ቡድን አቋቁሞ የሰው፣ የሰነድ፣ የእግዚቪት ማሰረጃ በማሰባሰብ በተከሳሽ ላይ የወንጀል ምርመራ አጣርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ በተከሳሽ ላይ አስር ክሶችን መስርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቷል፡፡
በ25/4/2015ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ባቀረበው የመከላከያ ምስክር የዐቃቤ ሕግን ክስ እና ማሰረጃ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል በማለት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ ተልጧል።አስ