አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም፡- በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ምስራቅ መሰቃን ወረዳ በታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት ሰባት ሰዎች መሞታቸው እና በርካቶ መቁሰላቸው ተገለጸ፤ የአከባቢው ነዋሪዎች መንግስት ጣልቃ በመግባት ግጭቱን እንዲከላከልላቸው ጠይቀዋል።
ሶስት የአከባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት ግጭቱ የተከሰተው ከአዲስ አበባ በ135 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኝ እና ዲዳ ተብላ በምትጠራ አከባቢ ቅዳሜ ሐምሌ 22 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ገልጸዋል።
ግጭቱ ከተከሰተበት አቅራቢያ የሚኖር የአከባቢው ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድር እንደገለጸው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች ከዲዳ ከተማ ወደ ኢንሴኖ ከተማ ገበያ ቀንን ምክንያት በማድረግ ሲጓዙ በነበሩ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። ወደ ኢንሴቦ የቅዳሜ ገበያ በጋሪ እና በባጃጅ ይጓዙ በነበሩት የዲካ ነዋሪዎች ላይ በማረቆ አከባቢ የሚገኙ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው እንደገደሏቸው ገልጸዋል።
ሌላኛው የአከባቢው ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቀው ነዋሪዎቹ በጉዞ ላይ እያሉ አስቁመው እንዳስወረዷቸው እና በቅርብ እርቀት ላይ ሁነው በመተኮሱት ጥይት ሰባት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውን ገልጸዋል። በጥቃቱ ምክንያት ከተገደሉት መካከል ከባሏ ጋር በመጉዋዝ ላይ የነበረች እርጉዝ ሴት እንደምትገኝበት ነዋሪው ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።
ሌላኛው ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአከባቢው ነዋሪ በስልክ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ተመሳሳይ የታጣቂዎች ጥቃት በአከባቢው እየተለመደ መምጣቱን ገልጸው ባለፈው ሳምንት ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት ባል እና ሚስት ከጎረቤታቸው ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን በአብነት ጠቅሰዋል። በአከባቢው እየተስተዋለ ያለው የታጣቂዎች ጥቃት ፍርሃት እና አለመረጋጋት እየፈጠረ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። ለግጭቱ ዋነኛ መንስኤ ለረዝም ግዜያት በዞኑ በመሰቃን እና በማረቆ ወረዳዎች መካከል ያለው የድንበር ችግር መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። አስ