ዜና፡ በአማሮ ልዩ ወረዳ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ የአራት ሰዎች ህይወት በኮሌራ በሽታ ምክንያት ማለፉን የልዩ ወረዳው ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4/2015 ዓ.ም፡- በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ የአራት ሰዎች ህይወት በኮሌራ በሽታ ምክንያት ማለፉን የልዩ ወረዳው ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዋና ሥራ ሂደት የማህበረሰብ ተግባቦትና አጠቃላይ ጤና ኤክስቴንሽን አስተባባሪ አክሊሉ ካለብ በሽታው የተዛመተው ከአጎራባች  ወረዳዎች እንደሆነ ጠቅሰው ከሞያሌ ተነስቶ አጣድፎት በቡርጂ ጤና ጣቢያ ደርሶ ህክምና ላይ የነበረው አንድ ወጣት ህይወት ማለፉን ገልጸዋል።

ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ የአራት ሰዎች ህይወት በኮሌራ በሽታ ምክንያት ማለፉን የተግባቦትና የኤክስቴንሽን ዘርፍ አስተባባሪ የገለፁ ሲሆን የኮሌራ በሽታ ሆኖ ከታወቀ ከሜያዚያ 30 ጀምሮ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የልዩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በሜያዚያ 30/2015 ዓ.ም፣ ከጋላና ወረዳ መጣሬ ኮምቦልቻ ቀበሌ ወደ ኬሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የገቡ ሁለት ታማሚዎች ተረባርበው ህክምና በመስጠታቸው ህይወታቸው ልታርፍ መቻላቸውን አስተባባሪው ገልፀው፣ ጤንነታቸው ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ከሜያዚያ 2/2015 ጀምሮ በወረዳችን በዬሮና ጋና ቀበሌ መሀከል በሽታው ተከስቶ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የተናገሩት አቶ አክሊሉ፣ ሌሎች ሁለት ሰዎች ግን የህክምና እርዳታ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በቅርበት ላይ የነበሩ የኢታቴና ድርባ ጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ ርብርብ ብያደርጉም ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል።

ሕዝቡን ለማዳን ከልዩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የባለሙያዎች ቡድን አስፈላጊውን የሕክምና መድሐኒትና ቁሳቁሶችን ይዘው ወደ አካባቢያቸው ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ የተግባቦትና የኤክስቴንሽን ዘርፍ አስተባባሪ አስታውቋል።

ማህበረሰቡ የግልና የአከባቢውን ንጽሕና በመጠበቅ ረገድ ላይ ጉልህ ሚና እንድጫወቱ ያሳሰቡት ባለሙያው፣  ጥሬ የሆኑ ምግቦችን በተለይ ፍራፍሬዎች ቀቅሎ በመመገብ በሽታው እንድከላከሉና ነገሮችን ሁሉ በጥንቃቄ ማድረግ ይጠብቅባቸዋል ብለዋል። ዉሃ ካፈሉ በኋላ አቀዝቅዞ መጠጣት፣  ከታመመው ሰው ራሱን በመጠበቅና ትኩስ ወተትም ቢሆን አፍልቶ መጠቀም የሁሉም ዜጎች ግዴታ እንደሆነ አጥብቆ አስተባባሪ አሳስበዋል።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.