ዜና፡ በትግራይ የተፈጠረው ሰላም ዘላቂነት የኤርትራ እና ከመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ውጭ ያሉ ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ አሜሪካ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም፡- በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ስድስት ወራት መሙላቱን ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መግለጫ ሰጥተዋል። አንቶኒ ብሊንከን በመግለጫቸው በትግራይ የተጀመረው ሰላም ዘላቂ እንዲሆን የኤርትራ እና ከመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ውጭ ያሉ ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል። በተጨማሪም በፌደራል መንግስቱ እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በታንዛንያ ድርድር መጀመሩን አወድሰዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት ተግባራዊነት ላይ ሁለቱም ሀይሎች ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቋል። የመሰረታዊ አገልግሎቶች መጀመር፣ የሰብአዊ ረድኤት አቅርቦት መሻሻል፣ የህወሓት ሀይሎች ከባድ መሳሪያዎችን ማስረከባቸው፣ በእስር ላይ የነበሩ መለቀቃቸው፣ ሁሉን አካታች የሆነ የሽግግር ሂደት ለመከተል የተጀመረው ሂደት እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረቱን መስሪያቤቱ በመግለጫው ከጠቀሳቸው ውስጥ ይገኙበታል።

በትግራይ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከፌደራል መንግስቱ ውጭ ያሉ ታጣቂዎች እና የኤርትራ መንግስት ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ ማድረግ እንዲሁም ተአማኒነት ያለው፣ ጥፋተኞችን ተጠያቂ የሚያደርግ የሽግግር ፍትህ ማስፈን ቁልፍ መሆኑን አመላክቷል።

በሰሜን ኢትዮጵያ የታየው ስኬታማ የሰላም ሂደት በኦሮምያ ሰላም ለማምጣት ትልቅ እድል መፍጠሩን መግለጫው ጠቁሟል። የአሜሪካ መንግስት በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል በታንዛንያ ድርድር መጀመሩን እንደሚያወድስ ያስታወቀው መግለጫው ድርድሩ ሁሉቱንም ሀይሎች ሊያግባባ የሚችል መፍትሄ ይዞ ይመጣ ዘንድ በቅንንት እንዲደረግ አሳስቧል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.