ዜና፡ በትግራይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ በአክሱም ጽዮን የጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/2015 ዓ.ም፡- በትግራይ ክልል የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ እና በትግራይ ክልል በሚገኙ የእምነቱ አባቶች በመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መካከል የተፈጠረው ልዩነት ባልተፈታበት ሁኔታ የትግራይ አባቶች ሹመቱን ለማካሄድ መወሰናቸውን ለመገናኛ ብዙሃን በላኩት ደብዳቤ አስታውቀዋል። የሚዲያ ሽፋን በጠየቁበት ደብዳቤ እንደተመላከተው በእለቱ የአስር ጳጳሳት ሹመት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት በትግራይ ጉብኝት ያካሄዱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በክልሉ ጉብኝት ቢያካሂዱም በክልሉ ከሚገኙ የቤተክርስቲያኗ ብጹአን አባቶች ጋር ተገናኝተው አለመምከራቸው ይታወሳል። አቡነ ማትያስ በመቀሌው ጉብኝታቸው ከክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ግዜያዊ አስተዳደሩ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደገለጹላቸው በዘገባችን  ተካቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.