ዜና፡ በተደጋጋሚ በሚከሰተው ድርቅ ክፉኛ መጎዳታቸውን የሶማሌ ክልል የዳዋ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ፣ ረሃብ የሰው ህይወት መቅጠፍ ጀምሯል

በመድሃኔ እቁባሚካኤል @Medihane

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28/ 2015 ዓ.ም፡– በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን በተከሰተው ከፍተኛ ድርቅ በርካታ ሰዎች ተጊጂ መሆናቸውን፣ እንስሳት እየሞቱ መሆኑን፣ ወንዞችም ሆነ የውሃ ጉድጓዶች መድረቃቸውን፤ ሰዎችም መሞት መጀመራቸውም ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፁ፡፡

በዞኑ በሚገኙ አራት ወረዳዎች ሞያሌ፣ ሁዴት፣ ከደዱማ እና ሙባረክ የሚኖሩ አርብቶ አደሮች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተመለክቷል። አሊ ኢብራሂም የተባለ የሞያሌ ወረዳ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቀው የዳዋ ዞን በክልሉ ከሚገኙ ሌሎች ዞኖች በከፋ ሁኔታ በድርቅ ቢጎዳም ትኩረት አላገኘም ብሏል። የድርቁ ሁኔታ እንስሳቶቻችንን ከመግደል ባለፍ አቅመ ደካማ ሽማግሌዎችን እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያጠቃቸውን ህጻናት ህይወት ያሳጣ ጀምሯል አስታውቋል። የሰዎች ሞት በዞኑ ሁለት ወረዳዎች መከሰቱን የተመለከ ሪፖርት መደረጉን ጠቁሟል።

አሊ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው በቅርቡ በድርቁ ሳቢያ አንድ ሽማግሌ መሞታቸውን እኔ ራሴ መረጃው ደርሶኛል ብሏል። አሎ ሁሉቆ በተባለች መንደር የሞቱትን ሽማግሌ ቀብር የሚያሳይ የፎቶ መረጃ ለአዲስ ስታንዳርድ ልኮልናል። የሽማግሌውም ሞት በድርቁ ሳቢያ መሆኑን አስረግጦ ገልጿል።

የውሃ ጥም በመቋቋም የሚታወቀው ግመል በድርቁ ሳቢያ ከሞተ ድርቁ ለሰዎች የሚፈጥረውን አደጋ ለመገመት አስቸጋሪ አይመስለኝም ብሏል። የአከባቢው ነዋሪዎች ግመሎቻቸው እና አህዮቻቸው ስለሞቱባቸው የትም ቦታ ሂደው ጠብታ ውሃ እንኳን ማምጣት አለመቻላቸውን አስታውቋል።

በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል አንዷ የሆነችው ሁዴት ወረዳ ነዋሪ ሞሃመድ ሰሙ የተባሉ የእድሜ ባለጸጋ በበኩላቸው ከአንድ መቶ ሺ በላይ የሚሆነው በአርብቶ አደርነት የሚተዳደረው የዞኑ ነዋሪ ግመሎቹን እና ከብቶቹን ማጣቱን ገልጸው ወደ ሁለት መቶ ሃያ ሺ የሚጠጉ እስሳት በድርቁ ሳቢያ መሞታቸውን እና ሌሎች ሰባት መቶ አርባ አራት ሺ የሚሆኑ እንስሳት የሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በቂ እርዳታ ካልተደረገላቸው በሞት አፋፍ ላይ ያሉ እንስሳቶቻቸውን እንዳያጡ ስጋት እንዳላቸው የእድሜ ባለጸጋው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

በዞኑ ያለውን አስከፊ ድርቅ ያገናዘበ እርዳታ እየደረሰን አይደለም ያሉት ሞሃመድ ሰሙ ለሽማግሌዎች ብቻ የሚበቃ ባለፉት ሶስት እና አምስት ወራት ሁለት ሁለት ኪሎ እህል መሰጠቱን ጠቁመዋል። እንጨት በመልቀም እና በማክሰል ወደ ከተማ በማቅናት በመሸጥ እና የቀን የጉልበት ስራ በመስራት የአከባቢው ነዋሪ ሂወቱን ለማትረፍ እየጣረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሙባረክ ወረዳ በኢትዮ ኬንያ ድንበር የምትገኝ ሲሆን በአከባቢው የሚፈሰው ዳዋ ወንዝ ለወረዳዋ ነዋሪዎች የሁሉም ነገራቸው ምንጭ ነው። የአከባቢው ነዋሪዎች ወንዙን ተገን አድርገው የመጣውን ድርቅ ሳይፈናቀሉ ለመቋቋም ከፍተኛ ግብግብ ማድረጋቸውን የወረዳው የአደጋ ስጋት አስተባባሪ ጀላኒ ሁሴን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸው ወንዙ መድረቁ ብቻ በአከባቢው የተከሰተው ድርቅ መጠን ገላጭ ነው ብለዋል። የአከባቢው ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑት ነዋሪዎች አርብቶ አደሮች መሆናቸውን የገለጹልን አስተባባሪው ሰማኒያ በመቶ የሚሆነት እንስታቶቻቸው መሞታቸውን ነግረውናል።

የዳዋ ዞን የአደጋ ስጋት አስተዳደር አብዲረሺድ ኢብራሂም አደን በበኩላቸው በአከባቢው የተከሰተው ድርቅ ከሶስት መቶ ሰላሳ ሺ በላይ እንስሳትን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ መግደሉን አስታውቀዋል። ስድስት መቶ አርባ ሺ የሚጠጉት እንስሳት በግጦሽ እጦት በሞት አደጋ ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል። በዞኑ ዪጠጉት አራቱም ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት መፈጠሩን ያስታወቁት አብድራሺድ ዞኑ ወሃ ለማከፋፈል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ነግረውናል። ድርቁ እና የኮሌራ ስጋት በዚሁ ከቀጠለና ትኩረት ተሰጥቶት በቂ ድጋፍ ካልተደረገ ትምህርት ቤቶችም ሊዘጉ ይችላሉ ሲሉም ስጋታቸውን አጋርተውናል።

በተጨማሪም ለአዲስ ስታንዳርድ የተላኩ ምስሎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ በአከባቢው የተከሰተው ድርቅ ዳፋ ለዱር እንስሳቱም ደርሷል። እጅግ የተዳከሙ በአከባቢው ከሚገኘው ገራይሌ ብሔራዊ ፓርክ የወጡ የዱር እንስሳት በየአከባቢው ይታያሉ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.