አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8/2015 ዓ.ም፡- ወደ ጎረቤት ሱዳን የተሰደዱ የትግራይ ተወላጆች በሀገሪቱ በተፈጠረው ጦርነቱ ሳቢያ ለከፋ ስቃይና መከራ መዳረጋቸውን የእንግሊዙ ተነባቢ ጋዜጣ ጋርድያን ይዞት የወጣ ዘገባ አስታውቋል። በሱዳን በተባበሩት መንግስታት መጠለያ ካንፕ የሚኖሩ ተጋሩ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ታፍነው በመወሰድ ላይ መሆናቸውን እና ቤተሰቦቻቸው ማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ለማድረግ ከፍተኛ ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው ዘገባው አመላክቷል።
ለጥቂት ግለሰቦች በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማጋበሻ በማገልገል ላይ ያለው የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሳቢያ በቀውስ ውስጥ በምትገኘው ሱዳን ተጠልለው የሚገኙ ተጋሩ ሌላኛዋ ሲኦል እየሆነችባቸው እንደምትገኝ ጋርድያን በዘገባው አትቷል።
የህገወጥ ሰዎች ዝውውሩ ኔትወርክ በሱዳን የትግራይ ስደተኞች መጠለያ ከሆኑት ኡምራኩባ እና ቱናይድባህ ጀምሮ እስከ ሊቢያ እንደሚደርስ የጠቆመው ዘገባው ከመጠለያ ጣቢያዎቻቸው ያለፈቃድ የወጡ እና በሱዳን ፖሊስ የተያዙ ስደተኞችን የሱዳን የፖሊስ አባላት አሳልፈው ለህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ እንደሚሸጧቸው አስታውቋል።
በሱዳን ስለሚገኙ የትግራይ ስደተኞችን አስመልክተው የረድኤት ድርጅቶች ከተባበሩት መንግስታት ተወካዮች ጋር መምከራቸውን በሱዳን የሚገኙ ምንጮቹ እንደነገሩት የገለጸው ዘጋርድያን ምንም አይነት እርምጃ አለመወሰዱን አመላክቷል።
የህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ አስገድዶ መድፈር እና ግርፋትን ጨምሮ ብዙ ግፍና መከራ እንደሚያደርሱባቸው መናገራቸውን ዘገባው አካቷል። አስ