አዲስ አበባ ፣ ታህሳሰ 8/2014 -በአዲስ አበባ ውስጥ በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን ፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የታሪፍ ማሻሻያን ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በሚኒባሶች የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛው 1 ብር ሲሆን፣ ከፍተኛው ደግሞ 2 ብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም በሚኒባስ (ቅጥቅጥ ወይም ሃይገር ባስ) የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በሚኒባስ በኪሎሜትር ከ40 ሳንቲም ወደ 45 ሳንቲም ከፍ የተደረገ ሲሆን፣ በታክሲ ደግሞ በኪሎሜትር ከ90 ሳንቲም ወደ 1ብር ከፍ ብሏል፡፡
በታክሲ ላይ የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛ 50 ሳንቲም ሲሆን ፣ከፍተኛው ጭማሪ 3 ብር ከ50 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡ ጭማሪው የኪሎ ሜትር ርቀትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡የታሪፍ ጭማሪው የተደረገው የነዳጅ ጭማሪን ታሳቢ ተደርጎ ነው፡፡ አ.ስ