ዜና፡ ምርጫ ቦርድ አዲስ ክልል ለመመስረት ህዝበ ውሳኔ እየተካሄዳ ባለበቅ ቀን በጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ለአራተኛ ጊዜ ስራ የማቆም አድማ እያደረጉ ነው

ጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ማዕከል፣ ዶይሳ ቀበሌ፣ ዶይሳ ምርጫ ጣቢያ ፤ ድምፅ የመስጠት ሂደት -ፎቶ፤ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ፣ጥር 29/ 2015 .ም፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በደቡብ ብሔር ህዝቦች ክልል መንግስት ስር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዮ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሄደው ህዝበ ውሳኔ የመረጮች ድምፅ እየተሰጠበት ባለበት ቀን ወልቂጤ ከተማን ጨምሮ  በጉራጌ ዞን ለእንድ ቀን የሚቆይ አራተኛ ዙር ስራ የማቆም አድማ እየተደረገ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

የጉራጌ ዞን የክልል አደረጃጀት ጥያቄን ተከትሎ በተነሱ ተቃውሞዎች ዞኑ ከህዳር 16 ቀን ጀምሮ በተደረጃ ኮማንድ ፖስት እንድትመራ አድርጓታል፡፡ ዛሬ እየተደረገ  ያለው ቤት የመዋል ተግባር ኮማንድ ፖስቱ ያስተላለፈውን ክልከላ በመጣስ ነው።

የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ሃይደር ሙራድ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፀው የጉራጌ ህዝብ በምክር ቤት የጠቀውን በክልል የመደራጀት መብቱን መንግስት በፍጥነት መልስ መስጠት ባለመቻሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በተደጋጋሚ ስራ የማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በወልቂጤ ከተማ ውስጥ በደቡብ ክልል ልዩ ሃይሎች እና ከአንቡላንሶች ውጭ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እየተደረገ አለመሁንን ሃይደር ገልፀዋል፡፡

ዘሬ እየተደረገ ያለው ስራ የማቆም አድማም በውልቂጤ ከተማ ብቻ ሳይሆን ጉሙሬ፣ እንደብር፣ አገና፣ ጉንቹሬ፣ ሚቄ፣ ዱንኩላ፣ ቋንጤ፣ አበሽኬ እና በሌሎችም ወረዳዎችም ቤት ውስጥ የመዋል አድማ  እየተከናወነ እንደሚገኝ ትግሉን ከሚመሩት አንዱ የሆኑት አንድነት አኑሎ  ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡ አክለውም ከነገ ጅምሮ ህዝቡ ወደ ተለመደው እንቅስቃሴ እንደሚገባ ጠቅሰው መንግስት ለጥያቄያችን መልስ እስካልሰጠ ድረስ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ትግሉ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፌደሬሽ ምክር ቤቱ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሚገኙ 6ቱ ዞኖች እና በአምስት ልዩ ወረዳዎች ”የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የመመስረት ጥያቄ  በማቅረባቸው ውሳኔ ለመስጠት እንዲያስችል በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ በዛሬዋ እለት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ህዝበ ውሳኔ እያካሄደ ይገኛል፡፡አስ

እንደ ምርጫ ቦርድ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጋሞ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጌድኦ፣ኮንሶ አና በደቡብ ኦሞ ዞኖችና በአምስቱ ልዩ ወረዳዎች  ማለትም በቡርጂ፣ ማሮ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ እና አሌ ልዩ ወረዳዎች የሚካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ድምፅ ለመስጠት ተመዝግበዋል፡፡

ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚገኙ የ6 ዞኖች (የጋሞ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶ እና የደቡብ ኦሞ ዞኖች) እና የ5 ልዩ ወረዳዎች(የቡርጂ፣ የአማሮ፣ የደራሼ፣ የባስኬቶ እና የአሌ ) በአንድ ክልል የእንደራጅ አቤቱታን ተቀብሎ ከመረመረ በኃላ በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ማስተላለፉ  ይታወሳል፡፡

ጉራጌ ዞንን ጨምሮ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ፣ ስልጤ እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አንድ ላይ አንድ ላይ እንዲቀጥሉ ውሳኔ አስተላልፏል። 

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት፤ ነሐሴ 5፤ 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ እድርጓል፡፡

የጉራጌ ዞን በደቡብ ክልል ከሚገኙ መዋቅሮች ውስጥ የ“ክላስተር” አደረጃጀትን አልቀበልም በማለት እራሱን የቻለ ክልል ለመመስረት  በተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረበ ነው። 

የክላስተር አደረጃጀትን በመቃወም በጉራጌ ዞን የተደረገውን ስራ የማቆም አድማ ተከትሎ በርካታ ሰዎች በፖሊስ ሃይሎች ለድብደባ እና ለእርስ የተደረጉ ሲሆን ድርጊቱ የዞንን ባለስልጣናት እና አስተባባሪዎች ላይ ያነጣጠረ ነበር፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.