ዜና፡ ልዩ ሃይሉን መልሰን የምናደራጅበት አላማ በወጉ ባላማስገንዘባችን ነው ህዝቡ ስጋት ያደረበት- የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4/ 2015 ዓ.ም፡- ልዩ ሃይሉን መልሰን የምናደራጅበት ምክኒያት ተጨማሪ ብቃት ያለው ሃይል ለመገንባት መሆኑን በወጉ ባላማስገንዘባችን ነው ህዝቡ ስጋት ያደረበት ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ ገለፁ፡፡ ብልፀግና በትኛውንም ጉዳይ ላይ ለመመካከር በሩ ክፍት ነው ያሉት ኃላፊው ተነጋግረን፣ ተወያይተን የሚጠቅመውን ልንወስድ ሲገባ በሃይል እና በጉልበት የከተማ ትጥቅ መሰል ጥፋቶች መከናወኑ ተገቢ አይደለም ሲሉም ገልፀዋል፡፡

አቶ ግርማ ይህንን ያሉት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከከልሉ ሚዲያ ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት ሲሆን ልዩ ሃይሉ በተለያዩ አደረጃጀት ውስጥ ሲገባ ከነበረበት ይበልጥ ለክልሉ፣ ለሀገሩ የደህንነትና ለፀጥታ ተቋማት ብቃት ያለው ሃይል ሆኖ እንዲያገለግል ስለሚሰራ በህረተሰቡ ዘንድ የሚነሱት ስጋቶች እውነት የሚመስሉበት የተለያየ መንገዶች ቢኖርም ነገር ግን ትክክል አይደለም ብለዋል፡፡

ልዩ ሃይሉን የመበተን ሳይሆን መልሶ የማደራጀት ስራ ነው እየተሰራ ያለው የሚሉት ሃላፊው በዚህ ውሳኔ ህዝቡ የተፈጠረበት ስጋት ትክክል ነው ባንልም ስጋት መነሳቱ ግን ተገቢ ነው ብለን እናምናለን ብለዋል፡፡ ነገር ግን የህዝቡ ስጋት ሁኔታውን የመራንበት መንገድ አሁናዊ መፍትሄውን የተዛባ አድርጎ እንዲመለከቱት ያደርጋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

“ልዩ ሃይሉን መልሶ የማደረጀቱ ስራ የዘገየ ነው፣ ሀይሉ ብሔርን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ቢቀጥል ከመልካምነቱ ይልቅ ለሀገራዊ ስጋትነቱ እየሰፋ ሊመጣ እንደሚችል ምልክቶች ታይተዋል” ሲሊ ተናግረዋል፡፡

ልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀት ተግባሩ ከግዜ አንፃር ተገቢ ቢሆንም በአተገባበር ደረጃ በአማራ ክልል ለየት ያሉ ችግሮች ገጥሞታል ያሉት አቶ ግርማ አፈፃፀሙ ዝርዝር እቅድ ወጥቶለት እንዲተገበር ሲደረግ በአማራ ክልል ስራውን እንዲያከናውን የተደራጀው ሃይል የተከተለው መንገድ ስህተቶች ነበረበት ብለዋል፡፡

ስህተቶቹንም ሲዘረዝሩ፣ “የመጀመሪያው ስህተት ልዩ ሃይሉን የማደራጀት ስራ እንሰራለን ስንል “ልዩ ሃይሉን ለማፍረስ መንግስት ወሰነ” የሚል የፖለቲካ ስራ በስፋት መሰራጨቱ ነው፤ ሁለተኛው ልዩ ሀይሉ እየተጠቀማቸው ያለው የጦር መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ ግብዓቶችን በተመለከተ ተጥቅ ሊፈታ ነው በሚል መዛባቱ ነው፤ ሶስተኛው ልዩ ሀይሉ እንደገና ሲደራጅ በዋንኛነት የክልሎችን የፀጥታ ተቋም እንደሚያጠናክር ሳይሆን ወደ መከላከያ ግባ እንደተባለና የመከላከያ ሀይል በጉልበት እንደሚያፈርሰው ተደርጎ መነገሩ ነው” ብለዋል፡፡

ትግበራው ላይ በክልሉ ውይይት ሲደረግ ከስራ አስፈፃሚዎች መካከል ትጥቅ እንዲያወርድ የሚል ደብዳቤ ባልታወቀ መንገድ ሾልኮ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ልዩ ሃይሉ በማየቱ ለምን ሳልወያይ ይህ ተወሰነብኝ በማለት መቆጣቱን ገልፀዋል፡፡ አክለውም “ልዩ ሃይሉ መቆጣቱ ትክክል ቢሆንም የእሱ አመራሮች ግን ተወያይተዋል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ልዩ ሀይል የመንግስትን ትዕዛዝ ባለበት ሆኖ እየተጠባበቀ ነው ያሉት ዘቶ ግርም ነገር ግን በተሰራጨው ደብዳቤ ጥቂት የተደናገጡት ክፍለ ጦሮች ተበትነዋል ብለዋል፡፡

የልዩ ሀይል አደረጃጀት ለአማራ እና ለሀገሪቱ እንደማይጠቅም ሲሰብኩ የነበሩ አካላት ብልፅግና መስራት ሲጀምር የሚያመጣውን ህበረተሰባዊ ዳፋ ሳይገነዘቡ ለፖለቲካ አላማቸው ሲሉ ባደረጉት እንቅስቃሴ አተገባበሩን በሰከነ መንገድ እንዳንሰራ ችግር ቢፈጥሩብንም ችግሩ ግን ይፈታል ብለዋል፡፡

ልዩ ሃይልን መልሶ የማደራጀት ውሳኔው የተወሰነው የሌሎች ሀገር ተሞክሮን መሰረት በማድረግ፤ ክልላዊ ፋይዳ ባለው ደረጃ እና ህጋሚ መሰረት ባለው መንገድ እንዴት እናደረጃቸው የሚል ጥናት ተከሄዷል ብለዋል፡፡ በጥናቱ ውጤትም አንድም ሀይል ሳንጥል ልንጠቀምበት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል፤ በዚህም መሰረት ውሳኔው ተወስኖ ወደ ተግባር ሲገባ ችግር የነበረው ጦርነት ውስጥ መግባታችን ነው እንጂ ለመተግበር ታቅዶ የነበረው ከዚህ በፊት ነበር ሲል ተናግረዋል፡፡

ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በክልሉ አመፅ ያስነሱ አካላት አሉ ያሉት አቶ ግርማ ማህበረሰቡ ለረጅም ጊዚያት በጦርነት ውስጥ በመቆየቱ ወደ ልማት እንጂ ወደ ጥፋት እንዳያመሩ የጥፋት ሀይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.