አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም. የደቡብ ክልል ኮማንድ ፖስት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ በጉራጌ ዞን ወረዳዎችና ከተማዎች ማንኛቸውም መንግስታዊ ይሁን መንግስታዊ ያልሆኑ ስብሰባዎች እና ዉይይት ማድረግ መከልከሉን አስታወቋል።
የክልሉ ኮማንድ ፖስት ከዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ሰልፍና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ እና የንግድ ሱቆችና ተቋማትን ያለምንም ምክንያት መዝጋት የከለከለ ሲሆን የባጃጅ እንቅስቃሴ እስከ ምሽት 2 ሰአት ድረስ እንዲሁም የሞተር ሳይክል እንቅክቃሴ እስከ ምሽት 1ሰአት ብቻ እንዲሆን ገድቧል።
ኮማንድ ፖሰቱ በመንግሥት የስራ ሰአት የቢሮ ሀላፊም ይሁን ባለሙያ በቢሮ አለመገኘት እንደማይቻል ገልፆ ይህን ትእዛዝ በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።አስ