እለታዊ ዜና፡ የየመን አየርመንገድ በሳምንት ሁለት ግዜ ከየመን ኤደን ወደ አዲሰ አበባ በዛሬው ዕለት በረራ እንደሚጀምረ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8/ 2015 ዓ.ም፡– የየመን አየርመንገድ ከስምንት አመታት በኋላ በዛሬው ዕለት ከየመን ኤደን ወደ አዲስ አበባ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።

ከየመን ኤደን ወደ አዲስ አበባ በሳምንት ሁለት ቀናት በረራ እንደሚያደርግ የአየር መንገዱ የኢትዮጵያ ቀጠና ስራስኪያጅ የሆኑት ፋኡድ አታሽ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

የየመን አየር መንገድ ለመጨረሻ ግዜ ወደ አዲስ አበባ በረራ ያካሄደው ከስምንት አመታት በፊት መሆኑን ፋኡድ አውስተዋል። አየር መንገዱ በረራውን የሚያካሂደው በየሳምንቱ ረቡዕ እና አርብ መሆኑንን ገልጸዋል። ወደ አዲስ አበባ በረራ መጀመራችን ተጓዦቻችንን ወደ ተቀረው አለም ለማገናኘት የሚያስችለን ዋነኛ መሳሪያችን ይሆናል ብለዋል።

በረራውን አስመልክቶ አየር መንገዱ በይፋዊ የፌስቡክ ማህበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው ወደ አዲስ አበባ በረራ ማስጀመሩ አየር መንገዳችን በሙሉ አቅሙ እንዲንቀሳቀስ ለማስቻል እና የነበረውን የቀድሞ ደረጃ በድጋሚ እንዲያገኝ ለማስቻል ለሚደረገው ጥረት የመጀመሪያው እርምጃ መሆኑን አመላክቷል። በተጨማሪ የአየር መንገዱ አመራር በተለይም የቦርድ ሊቀመንበሩ ካፕቴን ናስር ማህሙድ እና የንግድ ጉዳዮች ማናጀሩ ማህሰን ሀይድራ የጋራ ትብብር ስኬት እና ተግባቦት ውጤት መሆኑን ጠቁሟል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.