አዲስ አበባ፣ ጥር፣ 2/2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ የተመራ ልዑካን ቡድን እንዲሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የትግራይ ተወላጅ አትሌቶችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት ወደ መቐለ አቅንተዋል።
ፌዴሬሽኑ እንዳስታወቀው የልዑካን ቡድኑ ዛሬ ማለዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ወደ መቐሌ አምርቷል።
ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ደራርቱ ለሀገር የወርቅ መዳልያ ያስገኙ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸውን እንዳያገኙ መንግስት እገዳውን እንዲያነሳ ተማጽናለች፡፡ “እንደምናውቀው የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች እስካሁን ቤተሰባቸውን የማግኘት እድል አላገኙም፡፡ ክቡር ፕሬዝዳንታችን በእርግጠኝነት ይህንን ችግር ይፈታሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ መንግስታችንም ይህንን ችግር ይቀርፋል ብለን እናስባለን” ስትል ደራርቱ በታላቁ ቤተ መንግሥት በተካሄደው የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ ተናግራለች።
“ለቀጣይ ውድድሮች በሙሉ ልብ የሚሰለፉ በትግራይ ክልል አትሌቶች ስላሉን ደስታችን ሙሉ እንዲሆን ይህ መሆን አለበት” ብላለች፡፡
በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአስተናጋጇ ከአሜሪካ በመቀጠል ኢትዮጰያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ እንድታጠንቅቅ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ከያዛቸው የትግራይ ሴት ተወላጅ አትሌቶች፤ ጎቲቶም ገብረስላሴ፣ ለተሰንበት ግደይ እንዲሁም ጉዳፍ ጸጋይ ግንባር ቀደሞቹ ነበሩ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አራት ወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት ነሐስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ያጠናቀቀ ሲሆን ሦስቱ ሴት አትሌቶች ከአራቱ የወርቅ ሜዳሊያዎች ውስጥ ሦስቱን ማስገኘታቸው ይታወሳል።
ለሁለት አመታት በትግራይ ክልል የነበረው ጦርነት የተነሳ አትሌቶቹ ከቤተሰቦቻቻው ጋር ሳይገኛኙ መቆየታቸው ደስታቸውን ሙሉ ሊያደርገው አለመቻሉን ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡
ምክነያቱ ባልታወቀ 16 እስከ 65 እድሜ ያላቸው ከመቐለ ወደ እዲስ አበባ ከእሉላ እባነጋ አለማቀፍ እየር ማረፍያ እንዳይወጡ በመከልከሌ የልኡካን ቡድኑ የተደረገ ጉዞ ግን ግኣ ሚያጋባ ነው።
የልኡካን ቡድኑ ወደ ትግራይ ያመራው እድሜያቸው ከ16 እስከ 65 የሆነ የትግራይ ተወላጆች ከመቐለ አሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ወደ አዲስ አበባ እንዳይመጡ በተከለከሉበት ወቅት ነው፡፡አስ