አዲስ ስለተቋቋመው የሸገር ከተማ አስተዳደር ምን ያህል ያውቃሉ ?

አዲስ አበባ፣ ጥር 2/2015 ዓ.ም፡- የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አምስት ከተሞችን ማለትም ሱሉልታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ገላን እና ሰበታን በአንድ አጣምሮ የሚያስተዳድር የሸገር ከተማ አስተዳደር እንዲመሰረት በቅርቡ መወሰኑ ይታወሳል።

ከተማው በ160 ሺህ ሄክታር ላይ የተመሰረተ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በማጣመር 12 ክፍለ ከተሞች እና 36 የወረዳ አስተዳደሮችን በአንድ ላይ አዋቅሯል፡፡

ሸገር ከተማ የተቋቋመት የመጀመሪያ አላማ የገበያ ማዕከልና መሠረታዊ ልማቶችን በማስፋፋት የኦሮሞ ህዝብ ከአዲስ አበባ እና ከአካባቢዋ ላይ ማግኘት ያለበትን ጥቅም እና መብት በጠንካራ መሰረት ላይ ለማኖር መሆኑ  ተገልጧል

በተጨማሪም ጽዱና የተሻለ መሰረተ ልማት መገንባት፣ ከህገወጥነት የፀዳ ሳቢ ከተማ መገንባት፣ ብሎም ኢንቨስትመንትን መሳብ ከአዲሱ ከተማ አስተዳደር ምስረታ ዋነኞቹ ግቦች ናቸውም ተብሏል፡፡ በቀጣይ 7 ዓመታት አዲሱ የሸገር ከተማ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ መያዙም ተነግሯል።

ከተሞቹን በአንድ ላይ የሚያስተዳድረው ከንቲባ ዋና መቀመጫው በአዲስ አበባ ነው፡፡

የሸገር ከተማ አዲስ ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛ በተለይም ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቆይታ የቀድሞ ልዩ ዞን መፍረስ እና የአዲሱ ከተማ ምስረታ አስፈላጊነት ቀደም ሲል በልዩ ዞን ስር ገብተው የነበሩ ከተሞች ሰፊ የማልማት እቅድ ቢያዝላቸውም በታሰበው ልክ ከመሄድ ይልቅ ለህገወጥ ግንባታ እና መሰረታዊ የአገልግሎት ቅልጥፍና ችግር መጋለት ሌላ አማራጭ በማስፈለጉ ነው ሸገር ከተማ የተመሰረተው ብለዋል፡፡

ይህንንም ያሳካ ዘንድ በትላንትናው እለት የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተመስርቷል፡፡ በምስረታውም፣ አቶ ቃበቶ አልቤን የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል። ወይዘሮ ጸሐይ ደበሌ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ተሰይመዋል፡፡ ምክር ቤቱ በማስቀጠልም ዶክተር ተሾመ አዱኛን የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል፡፡

የሸገር ከተማ ምክር ቤት የተቋቋመው ከከተማው መዋቅር  ጋር በተያያዘ በርካታ ተቃውሞዎች እየተሰሙ ባለበት ወቅት ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ልዩ ዞን ፊንፊኔ ዙሪያ በባራቅ ወረዳ የሚገኙ ቀበሌ ነዋሪዎች በከተማው ስር ባለመካተታቸው የተቋውሞ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡

በበራቅ ወረደ ከሚገኙ ቀበሌ ውስጥ አስሩን በሸገር ከተማ ስር አስገብተው 13 የሚሆኑ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ስር እንዲተዳደሩ አድረገዋል በማለት ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን የ13ቱ ወረደ ነዋሪዎች የአስተዳደር አግልግሎት ለማግኘት 200 ኪ.ሜ በመጓዝ ፊቼ ከተማ መሄድ ግድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አክለውም መንግስት ስለ ሸገር ከተማ ምስረታ ከነዋሪዎቹ ጋር እንዳልተመካከረ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የሰበታ ሃዋስ ወረዳ ነዋሪዎችም 24 የሚሆኑ ቀበሌዎች በሸገር ከተማ አስተዳደር ስር ለመካተታቸው ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

የሸገር ከተማ ምስረታ ላይ ቅሬታ ያቀረቡት ነዋሪዎች ብቻ አይደሉም፡፡ የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ፣ የከተማ ምስረታ ግልፅነት የጎደለው እና ህጋዊ ሂደቶችን ያልተከተለ ነው በማለት በግንባር ቀደምነት ቅሬታ ሲያቀርቡ ከነበሩት አንዱ ናቸው፡፡

“ነዋሪዎቹ ያነሱት ቅሬታዎች የግንዛቤ ችግር ነው እንጂ ነገርየው ቅሬታ የሚያስነሳ አይደለም” ሲሉ የሸገር ከተማ አዲስ ከንቲባ ዶክተር ተሾመ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባው ዶ/ር ተሾመ አዱኛ የከተማው የማስተዳደር አቅም ታይቶ ጥያቄ የሚያነሱ አከባቢዎች ወደ ከተማው የሚካለሉበት አግባብ ሊፈጠር ይችላል ብለዋል ከዶቸ ቨለ ጋር ባደረጉት ቆይታ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን አዲሱ ከተማ ከዚህ በላይ የመስፋት አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ እንደሌሌውም አመልክተዋል፡፡

የአዲሱ ከተማ መዋቅር መዲናዋ ጋር የሚደጋገፍ እንጂ ምንም ጉዳት የማድረስ ውጥን የለውም ብለዋል፡፡ ይልቁንም ሁለቱ ከተሞች ተደጋግፈው ለነዋሪዎቻቸው ምቹ ሁኔታን ለማፍጠር አቅምና እድላቸው ይሰፋልም  ነው የተባለው፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.