አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም፡- በጉራጌ ዞን የቀቤና ብሔረሰብ ከዚህ በፊት የቀቤና ፅሑፍ ቋንቋን ሲገለገልበት የነበረው የሳባ ፊደል ከቋንቋው ባህሪ ጋር ባለመጣጣሙ እና ቋንቋው እንዳያድግ በማድረጉ ፅሑፍ ቋንቋውን ወደ ላቲን ፊደል ለመቀየር ተወስኖ ወደ ተግባር መገባቱ ተገለፀ፡፡
ይህ የተባለው የቀቤና ህዝብ ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ላይ ተመስርቶ በየአመቱ የሚዘጋጀው መርሀ-ግብር አካል የሆነው ሶስተኛ ሲምፖዚየም የቀቤናን የፀሁፍ ቋንቋን ከሳባ ወደ ላቲን በመቀየር ሂደት ዙሪያ ጥናት ቀርቦ ውይይት በተደረገበት መድረክ መሆኑን ፋና ዘግቧል፡፡
የቀቤታ ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ ሙሀመድ ሀሰን፣ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የሳባ ፊደል ማህበረሰቡ በፅሁፍ ለመግባባት ባለማስቻሉ፣ ለተማሪዎች ምቹ ባለመሆኑ እንዲሁም ቋንቋውን ለማሳደግ ባለማስቻሉ ፊደሉን ወደ ላቲን ፊደል መቀየር አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል፡፡
የኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልሳን መምህር እና ተመራማሪ ታደሰ ግርማ (ዶ/ር) ቀቤና የፅሑፍ ቋንቋ አንዳለነበረው እና ከአመታት በፊት በሳባ (የግዕዝ) ፊደል በመጠቀም ሲፃፍ እንደነበር ገልፀው ቋንቋው የደጋማ ቋንቋዎች የሚያሳዩት ባህሪዎች ጋር ባለመጣጣሙ እና ቋንቋው አንዳያድግ በማድረጉ ፊደሉ ወደ ላቲን እንዲቀየር ማህበረሰቡ ጥያቄ ባቀረበው መሰረት ጥናት መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ክልል ቤረሰቦች ምክር ቤት ባስጠናው መሰረትም ከፍተኛ የህዝብ ፍላጎት በመታየቱ ፊደላትን ወደ መለየትና የመማሪያ መፅሓፍትን ወደ መቅረፅ መገባቱም ተገልጧል፡፡ በተከናወነው ጥናት ማህበረሰቡ በሳባ ፊደሉ መግባባት ባለመቻሉ ከ90 በመቶ በላይ መቀየር አለበት የሚል ድምፅ በመገኘቱ ውጤቱ ለወረዳው ብሔረሰብ ምክርቤት ቀርቦ ፀድቋል ብለዋል ሙሀመድ ሀሰን፡፡ ቋንቋው ወደ ላቲን ፊደላት መቀየሩ ለቋንቋው እድገት ትልቅ አስቷፅኦ ያደርጋልም ተብሏል፡፡
መምህር እና ተመራማሪ ታደሰ የቀቤና ቋንቋ ድምጸቶችና ቋንቋው ውስጣ ያሉ ባህሪያት ተለይተው በምን አይነት ፊደል ቢወከሉ መፃፍ እንሚቻል በጥናታቸው ማሳየታቸውን ገልፀዋል፡፡አስ