አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/ 2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ ዞን በጃዊ ሆስፒታል በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ቅጥር ሰራተኛ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ግለሰብ በህክምና የእውቀት ችግር ምክንያት የሁለት ሰው ህይወት እንዲጠፋ በማድረጉ በ11ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 5,000 እንዲቀጣ ተወሰነ፡፡
ግለሰቡ የተመኝ አምላክ የተባለች የ7 ወር ህፃን እና የኔወርቅ ደሳለው የተባለችውን የ25 ዓመት ወጣት ለሞት የዳረገ መሆኑን የአዊ ብሔረሰብ ዞን ፍትሕ መምሪያ ገልጧል፡፡
በሀሰት ዶ/ር ጌትነት ወንድ አወቅ ተብሎ ሲጠራ የነበረው ይህ ግለሰብ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሜዲስን የዶክትሬት ዲግሪ እንደተማረ አስመስሎ በሆስፒታሉ የተቀጠረ ሲሆን 9056 ብር እየተከፈለው ሲሰራ መቆየቱም ተገልጧል፡፡
በመሆኑም የሰው ህይወት በማጥፋት፣ የሙስና ወንጀል መንግሥታዊ ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሀሰት መለወጥ ወይም በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ሙስና ወንጀል በዐ/ህግ ክስ ቀርቦበት በቀን 15/3/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ11ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 5,000 እንዲቀጣ ተፈዶበታል። አስ