ትኩስ ዜና: ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ግብዓት የፈሰሰበት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንፃ ከመመረቁ ጥቂት ቀናት በፊት በእሳት አደጋ መሰረተ ልማቱ ወደመ

ፎቶ: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር


አዲስ አበባ፣ ጥር 16/2015 ዓ.ም፡- በትናንትናው እለት ምሽት 4፡48 ላይ “ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ግብዓት የፈሰሰበት” የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንፃ ከመመረቁ ጥቂት ቀናት በፊት በደረሰበት እሳት አደጋ መሰረተ ልማቱ ወደመ፡፡

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መረጃ “የአደጋው ምክንያት እና መንስኤ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት ሲሆን ምርመራው እንዳለቀ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል፡፡”

ፎቶ: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና ሌብነትን ለመከላከል የዲጂታይዜሽን ስርዓትን ለመተግበር በርካታ ስራዎችን እያከናወነ” እንዳለ ይታወቃል ያለው አስተዳደሩ፣ በተለይም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የነበረውን ብልሹ አሰራር ሌብነትን ለማስተካከልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ይረዳ ዘንድ የዘመናዊ የቢሮ ግንባታና የተቋማዊ ሪፎርምና የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመተግበር ከንቲባዋ አስተባባሪነት የኢትዮ ቴሌኮም ፤ የአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ተቋማት የተሳተፉበት የዲጂታል አገልግት መስጠት የሚያስችል ስራ የፊታችን ቅዳሜ ለምረቃ የሚያበቃ ስራ በትጋት ተሰርቶ ነበር፡፡

ነገር ግን ህንፃው ትናንት ምሽት በደረሰበት እሳት አደ ወድሟል፡፡

“የአካባቢው ማህበረሰብ መንግስት የጀመረውን ጥረት ለመደገፍ ከዚህ አደጋ ጋር ተያይዞ ማንኛውንም መረጃዎች በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ” የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቕርቧል።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.