ትንታኔ፦ በልዩ ማዘዣ ወረቀት ብቻ እንዲሸጥ የሚፈቀደው የትራማዶል መድኃኒት ከልክ ያለፈ አጠቃቀም እና እያስከተለ ያለው ማህበራዊ ቀውስ

የአዲስ ህይወት የአልክሆል መጠጥና የአደንዛዥ ዕፅ የቅድመ መከላከልና የተጠቂዎች ማገገሚያ ማዕከል

በብሩክ አለሙ @Birukalemu21

አዲስ አበባ፣ጥቅምት29/ 2015 ዓ.ም ፦ በጥቅምት 22 ቀን የኢትዮጵያ የምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ባወጣው ማሳሰቢያ በኢትዮጵያ የሚገኙ መድሃኒት ቤቶች ትራማዶልን የተባለ ለአጭር ጊዜ እፎይታ የሚውል የኦፒዮይድ ዝርያ መድሃኒት ከመሸጥ እንዲቆጠቡ መመሪያ ሰጥቷል። ያለ ልዩ ማዘዣ በተጠቃሚዎች እንደልብ የሚሸጠው ይህ መድሃኒት፤ ከሀኪሞች ፈቃድ ውጭ በሽያጭ መልክ እንዳይቀርብ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ መሆኑን ባለሥልጣኑ ጠቅሷል። ባለሥልጣኑ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው ትራማዶል አለቅጥ በጥቅም ላይ መዋል የብዙዎችንት በተለይም የወጣቶችን ህይወት አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን የሚገልጹ ሪፖርቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመሩ በመምጣታቸው ነው።

ትራማዶል ከጤና ባለሙያ ትዕዛዝ ያለ ማዘዣ የመውሰድ ተግባር  እየተስፋፋ መምጣቱ አልፎ አልፎም በሃኪም  ከታዘዘው  መጠን አብዝቶ መውሰድ  ወይ ግዜን ጨምሮ መውሰድ  ለሱሰኝነት ያጋልጣል፡፡  በተለያየ ግዜየተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት ትራማዶልን መውሰድ አዕምሯዊ  ብቻ ሳይሆን  አከላዊ ሱስም እንደሚያስይዝ ያሳያሉ፡፡

ከአዲስ ስታንዳርድ ጋረ ቆይታ  ያደረጉ ባለሙያዎቸ እንዳሰታወቁት ትራማዶልን የሚጠቀሙ ወጣቶች ቁጥር እጅግ እየተበራከተ መምጣቱን  ገልፀው መንግስት በመድኃኒቱ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የማያደርግ ከሆነ ውጤቱ አስከፊ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ ትራማዶልን ከህክምና ዓላማ ውጪ መውሰድ ከፍተኛ የጤና ጉዳት ያስከትላል።

በተለይ ወጣቱን የሱስ ተገዠ  በማድረግ  አምራቹን የማህበረሰብ ክፍል በማደንዘዝ  ጤናማ ማህበረሰብ እንዳይገነባ ከፍተኛ መሰናክል እንደሚሆን  በመገንዘብ  የኢትዮጵያ ምግብና መደኃኒት ባለስልጣን ክትትል ከሚደረግባቸው መደኃኒቶች ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል።

ባለስልጣኑ ሰሞኑን  ለሚዲያዎች በሰጠው መግለጫ በትራማዶል መድኃኒት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልጾ   የጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች ብቻ በልዩ ማዘዣ ወረቀት   እንዲሸጥ መደረጉን አስታውቋል፡፡

እንደ ባለስልጣኑ መግለጫ የመድሃኒቱ ማዘዣ አሰጣጥ ላይ  ጥብቅ ቁጥጥር   እንደሚደረግ ተገለጿል።  መድሃኒቱን መጠቀም የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ከፍተኛ የራስ ምታት፣ የሰውነት ላብ፣ የአእምሮ እረፍት ማጣት፣ የእንቅልፍ  ችግር፣ የድካም ስሜትን አንደሚያስከትል

መግለጫው አያይዞም ወጣቶቹ በዚህ መድሀኒት ሱሰኝነት ከተለከፉ መድኃኒቱን መውሰድ ማቆም ስለሚቸገሩ ጤናቸ ከመቃወሱም በላይ በሸገሪቱ ማህበራዊ ቀውስ ስለሚያስከትል ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለተለያዩ ወንጀሎች ተጋላጭነትን ያስፋፋል። መድሃኒቱ በመድኃኒት ችርቻሮ መሸጫ ተቋማት ላይ በዘፈቀደ እንዳይሸጥ ባለስልጣኑ በተለያየ ጊዜ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በልዩ የመድኃኒት ማዘዣ ብቻ እንዲሽጥ ለሁሉም የክልል ጤና ተቆጣጣሪዎች እንዲያውቁት በማድረግ ጥብቅ ክትትል እያደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡

ለስድስት አመታት የትራማዶል መድሃኒት ጥገኝነት

ሀብታሙ ለስድስት አመታት የትራማዶል መድሃኒት ተጠቃሚ ነበር። በተደጋጋሚ ከመውሰዱ የተነሳመ በሱሰ ተጠምዶ አንደነበር ይናገራል። ባለ ትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን በትራማዶል መድኃኒት ሱስ ከተያዘ በኋላ ህይወቱ መመሰቃቀሉን ገልጧል፡፡

ሀብታሙ (ስሙ የተቀየረ) በሙያው ፋርማስስት ሲሆን ትራማዶል መድኃኒትን ለስድስት አመታት ተጠቅሟል፡፡በኋላም ሰውነቱ መድኃኒቱን በመላመዱ የትራማዶል ዝርያ የሆነውን ፔቲዲን የተባለውን መድሃኒት ጀምሮ ነበር።

ሀብታሙ እንደሚገልፀው መድኃኒቱን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ከሚሸጡ የመድኃኒት መደብሮች እና በጥቁር ገበያ ከሚሸጡ ሰዎች በመግዛት ነበር የሚጠቀመው

ሀብታሙ በአሁኑ ሰዓት “በአዲስ ህይወት የሱስ ተጠቂዎች ማገገሚያ ማከል” ውስጥ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል፡፡ ሀብታሙ መድኃኒቱን መጠቀም የጀመረው በራስ ምታት(ማይግሪን) ይሰቃይ ስለነበር ከህመሙ ለመላቀቅ ነበር፤ በኃላ ላይ ግን በትራማዶል ሱስ መያዙን ያስረዳል፡፡ መድኃኒቱ ህመም ቢያስታግስም ህመሙን ታክመህ መፍትሄ እንዳታገኝ ያደርጋል የሚለው ሀብታሙ በሂደትም ህይወትን ሊያሳጣ እንደሚችል ይናግል ፡፡

ለአብነት ያህል እጢ ያለበት ሰው የሚሰማውን ህመሙ ለማስታግስ ሲል ሁሌም መድኃኒቱን ይወስዳል። ለጊዜው ፋታ ያገኛል ቀስ ብቀስ ለህልፈተ ህይወት ሊያበቃ ይችላል።

ሀብታሙ እንደሚገልፀው መድኃኒቱን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ከሚሸጡ የመድኃኒት መደብሮች እና በጥቁር ገበያ ከሚሸጡ ሰዎች በመግዛት ነበር የሚጠቀመው።

መድሃኒት መውሰዱን ለማቆም የወሰነ ቢሆንም ያቁም ለማቆም በመቸገሩ ምክንያት በህገ ወጥ መንገድ ከሚሸጡ ግለሰቦች በድብቅ መውሰድ መጀመሩን ይናገራል። መድኃኒቱ በአንዳንድ ጫት መሸጫ ስፍራዎችም እንደሚገኝ ይናገራል፡፡

ሀብታሙ ይህንን መድኃኒት በመውሰዱና በሱስ በመያዙ ምክንያት ከቤተሰቡ እና ከአካባቢወ ማህበረሰብ ጋር የነበረው መልካም ግንኙነት ተበላሽትዋል፣ቸልተኝነት ሰፍኖበታል ለልጆቹ የአባትነት ፍቅር እንዳይሰጣቸው አደርጎታል። በአጠቃላይ ኑሮውን አናግቶታል።

መድሃኒቱ ባስከተለበት ህመም ምክንያት ቅዱስ ጳውሎስ አጠቃላይ ሆስፒታል በመግባት ክሁለት ወር ህክምና በኋላ ወደ አዲስ ህይወት የሱስ ተጠቂዎች ማገገሚያ ማእከል ገብቶ ለአንድ ሳምንት ክትትል ተደርጎለት አሁን በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እናዳለና ከመድኃኒቱ ሱስ መላቀቅ እንደቻለም ገልጧል፡፡

አክሎም በዚህ መድኃኒት በርካታ በርካታ ወጣቶቸ ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን አስታውሶ የመድኃኒቱ ተጠቃሚዎች ለሆኑ ሰዎች በሙሉ ለጊዚያዊ ጥቅም ብልው ህይወታቸውን አደጋ ላይ መጣል የለባቸውም ሲል አስገንዝብዋል፡፤

በሱስ ውስጥ ላሉ ሰዎች የአልችልምን መንፈስ ከውስጣቸው በማስወጣት በማገገሚያ ማእከል ድጋፍ ከሱስ መላቀቅ እንደሚቻል በማመን ጥቆማውን አካፍሏል፡፡ መድኃኒቱን ያለ ማዘዣ ወረቀት የሚሸጡ ሀላፊነት የጎደለው ስራ የሚሰሩ ፋርማሲዎችና በጥቁር ገበያ የሚሸጡ ግለሰቦችም በእኔ የደረሰው በሌሎች እንዳይደርስ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ተማፅኗል፡

በጳውሎስ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አስራት ሀብተ ጊዮርጊስ ለአዲስ ስታንዳርደ በሰጡት ሙያዊ አስተያየተ ትራማዶል የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ሲሆን በሃኪሞች ትዕዛዝ ባቻ የሚወሰድ በመድሃኒት መሸጫ መደብሮችም ያለ ማዘዣ መሸጥ የማይገባው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መድሃኒቱ ስሜት የማንቃት ባህሪ ስላለው በብዛት ሲወሰድ ሱስ በማስያዝ ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ እንደሚያስከትል ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም ትራማዶል እራስን መሳት እንዲሁም ጨጓራ ላይ ጫና በመፍጠርለህመም ይዳርጋል ብለዋል፡፡

የትራማዶል መድሃኒት መውሰድን በአንዴ ማቆም የሚፍጥረው ስሜት ለምቋቋም ስለሚከብድ ቀስ በቀስ የመድሃኒቱን መጠን በመቀነስ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋለ ያሉት ዶ/ር አስራት ጎን ለጎንም የስነ ልቦና ህክምና እገዛ እየተደረገላቸው ከሱስ እንዲላቀቁ ማድረግ እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

“የአዲስ ህይወት የአልክሆል መጠጥና የአደንዛዥ ዕፅ የቅድመ መከላከልና የተጠቂዎች ማገገሚያ ማዕከል” መስራች ሲስተር ይርገዱ ሀብቱ በማእከላቸው ውስጥ በጫት እና አልኮል እንዱሁም ትራማዶል እና ፕቲዲንን ጨምሮ በሌሎች አደንዛዥ እፅ የተጠቁ ሰዎችን ከሱስ እንዲላቀቁ የማድረግ ስራን እየሰሩ እንደሆነ ከአዲስ ስታንዳርድ በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

ትልቅ ተጽእኖ በቤተሰብ እና በሀገር ላይ

ማዕከሉ 12 አልጋዎች ያሉት ሲሆን በተመላላሽ የሚታከሙ ሰዎችም እንዳሉ የጠቆሙት ሲስተር ይረገዱ በማእከሉ ውስጥ በትራማዶል መድኃኒት ሱስ ተይዘው ክትትል እያደሩጉላቸው ያሉ ሰዎች እንዳሉ ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ብዙ ተማሪዎች በትራማዶል መድኃኒት የተነሳ እራሳቸውን ስተው እንደሚወድቁ ገልፀዋል፡፡

በአስራዎቹ እድሜ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ታዳጊዎች የትራማዶል ተጠቂዎች ናቸው ያሉት ሲስተር ይርገዱ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስልጠና በሰጠንበትወቅት እንደተረዳነው ችግሩ በጣም አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በትምህርት ቤቶች ውስጥ በጓደኞቻቸው ጫና በመድኃኒቱ ሱስ የተያዙ በርካታ ተማሪዎች መኖራቸውንም አስረድተዋል፡፡ ትራማዶል የሚወስዱ ተማሪዎች መድሃኒቱ የእንቅልፍ ጊዚያቸው ስለሚያዛባው በትምህርት ላይ የማንቀላፋት ችግር ይገጥማቸዋል፣ በትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ ያደርጋቸዋል፡፡

ትራማዶል የሚጠቀሙ ሴቶች ቁጥር አነስተኛ አይደለም የሚሉት ሲስተር ይርገዱ አንዳንዶቹ በወር አበባ ወቅት የሚሰማቸውን ህመም ለማስታገስ መድኃኒቱን እንደሚጠቀሙ እና መድኃኒቱን ያለ ሀኪም ማዘዣ ወረቀት ከሚሸጡ ፋርማሲዎች እና ከጥቁር ገበያ እንደሚገዙም ገልፀዋል፡፡

አዲስ ህይወት የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ስራውን የሚያከናውነው ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ሲሆን፤ የሱስ ተጠቂዎቹ መጀመሪያ በጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ማገገሚያ ማእከሉ እንዲገቡ በማደረግ የሚወስዱትን መድኃኒት መጠን ቀንሰው በመስጠት እንዲሁም የምክር አገልግሎት እየተሰጣቸው ከሱስ እንዲላቀቁ ይደረጋል፡፡

በሱስ የተያዙትን ከሱስ ውስጥ ከማስወጣት ይልቅ ቀድሞ መከላከሉ እንደሚቀል የሚናገሩት ሲስተር ይርገዱ በህረተሰቡ ላይ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ እነደሆነ ይናገራሉ፡፡

በሱስ የተያዙ ሰዎች ወንጀል ውስጥ የመሳተፍ እድላቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ገልፀው፤ የስራ ተነሳሽነትን በማጥፋት በግለሰቡ፣ በቤተሰብ እና በሀገር ላይ ትልቅ ተጽእኖ ያስከትላል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በ16 እና በ85 የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በማእከሉ ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ገልፀው በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች እራሳቸው መደበቅ አቁመው ወደ ማገገሚያ ማእከላት ገብተው እንዲታከሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዶክተር ናሆም ግሩም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ጠቅላላ ሃኪም እና መምህር ሲሆኑ በማህበራዊ ገፃቸው ትራማዶል በወጣቱ ላይ እያደረሰ ያለውን ተፅእኖ ለመቀነስ ባጋሩት መልእክት ለብዙዎች ግንዛቤ ፈጥረዋል፡፡

ዶ/ር ናሆም ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ትራማዶል በህክምና ባለሙያ ትእዛዝ መሰረት መጠቀም ግድ የሚል የመድኃኒት አይነት መሆኑን ጠቅሰው ሁለት አይነት አጠቃቀም እናዳለው ይናገራሉ፡፡ አንደኛው በባለሙያ ካታዘው መጠን እና ጊዜ በላይ ጨምሮ መጠቀም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለሱስ ግብአትነት በፈቃዳቸው ሲጠቀሙ ነው።

ዶክተር ናሆም አብዛኞቹ ሰዎች መድኃኒቱ ሱስ ውስጥ እንደሚያስገባ ሳያውቁ ለህመም ማስታገሻነት አላማ ብቻ ያለ ባለሙያ ትእዛዝ ለረጅም ጊዜ እየተጠቀሙ ሲመጡ ሳያስቡት ሱስ ውስጥ እንደሚያስገባቸውም ያስረዱተ

ዶክተሩ ትራማዶልን መጠቀም ከመጠን በላይ ደስታ (Euphoria) እንዲሰማቸው ማድረግ፣ ሀይል መስጠት እንዲሁም ጊዚያዊ ተስፈ እንዲሰማቸው ማድረግ፣ ግራ የመጋባት ስሜትና ለሌላ ሰው የማይሰማ ድምፅ እንዲሰማቸው የማድረግ ሃይል አለው ብልዋል።

“በመድኃኒቱ ሱስ የተያዙ ሰዎች ሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ከዚያም አልፎ ራሳቸውን አጥፍተው ይገኛሉ”

ዶ/ር ናሆም

መድኃኒቱ ከፍተኛ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት እንደሚያስከትልም ዶ/ር ናሆም ገልፀዋል፡፡ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ጨጓራ ህመም፣ የኩላሊትና ጉበት መጎዳት፣ የመጣል እና የመንቀጥቀጥ እንዲሁም ድብርት የመሳሰሉትን ተፅእኖዎች ያስከትላል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሱሱ የተጠቁ ሰዎች ለራስ፣ ለቤተሰብ እንዲሁም ለሀገር ሸክም የሚያደርግ ሲሆን ትምህርት ወይም ስራን በአግባቡ መከወን እንዳይችሉ ማድረግ፣ በወንጀሎች ላይ የመሳተፍ እድላቸው ከፍ እንዲል መድረግ እንዲሁም ጥንቃቄ የጎደለው ግኑኝነት በማድረግ ለኤች አይ ቪ እና የልተፈለገ እርግዝና እንዲከሰት የማድረግ እድሉ ከፍ ያለ እንደሆነ ዶክተሩ ይገልፃሉ፡፡

“በመድኃኒቱ ሱስ የተያዙ ሰዎች ሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ከዚያም አልፎ ራሳቸውን አጥፍተው ይገኛሉ” ያሉት ዶ/ር ናሆም መድኃኒቱን ከባለሙያ ትእዛዝ ውጪ መጠቀም ጎጂ በመሆኑ ወጣቶች መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል። ዶክተሩ አያይዘውም መድኃኒቱን አብዝተው የሚወስዱ ሰዎች እንደ ሄሮይን፣ ካናቢስ እና የመሳሰሉትን የመጠቀም እድላቸ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የህክምና ባለሙያዎችም በትራማዶል መድኃኒት ሱስ እንደሚያዙ ያነሱት ዶክተሩ የህክምና ስራ ከፍተኛ ድካም ያለው ሙያ በመሆኑ ከድካማቸው ለመላቀቅ መድኃኒቱን ሲወስዱ በሱስ እንደሚያዙም ገልፀዋል፡፡

የመድኃኒቱን ጉዳቶች አውቀው ይሁን ሳይውቁ በጓደኞቻቸው እንዲሁም በራሳቸው ግፊት ወደ ሱስ የሚገቡ ሰዎች ለከፋ ችግር የሚያገልጥ ሱስ መሆኑን በመገንዘብ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.