ትንታኔ፡ ሜታ ላይ የተመሰረተበት የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ክስ አካል የሆነው የኢትዮጵያዊዉ ፕሮፌሰር ግድያ እንዴት ተፈፀመ?

ፕሮፌሰር ማዕረግ አማረ አብረሃ ፡ ፎቶ አብረሃም ማዕረግ

   በመድሃኔ እቁባሚከኤል @Medihane

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11/ 2015 .ም፡ የአራት ልጆች አባት እና የ60 አመቱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አናሊቲካል ኬምስትሪ ፐሮፌሰር ማእረግ አማረ አብረሃ እ.አ.አ ህዳር 3/ 2021 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ በእኩለ ቀን በቤታቸው ፊት ለፊት በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ወንጀለኞቹ ጥለውት የሄዱት አስክሬን ማዘጋጃ እንዲነሳ ከማድረጉ በፊት በስፍራው ለሰዓታት ሳይነሳ ቆይቷል፡፡

ከዚህ ቀደም በታተመው በአዲስ ስታንዳርድ መፅሔት ላይ ልጃቸው አብረሃም ማዕረግ እንደፃፈው የፕሮፌሰሩ ግድያ የተፈፀመው ከ50 ሺ በላይ ተከታዮች ባለውና “BDU STAFF” በሚል የፌስቡክ ገፅ ላይ የስም ማጥፋትና የግድያ ዛቻ ከተለጠፈ በኋላ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት በኬንያ ናይሮቢ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሜታ ኩባንያ ላይ በቀረበው የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ክስ ላይ አብርሀም ከከሳሾች ውስጥ አንዱ ነው። ጉዳዩ ለትርፍ ባልተቋቋመው ፎክስግሎቭ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን በፌስቡክ ፈጣን እርምጃ ባለመውሰዱ የፕሮፌሰር ማዕረግ ህይወትን እጣ ፈንታ እንደለወጠው ምክንያታዊ ማረጋገጫ አለ ብሏል።

የፎክስግሎቭ ዳይሬክተር የሆኑት ሮዛ ከርሊንግ “ፖስቶቹ ወዲያውኑ ተነስተው ቢሆን ወይም በማጣሪያ ታይተው ቢነሱ ኖሮ ፕሮፌሰሩ በህይወት ይኖራሉ ብለን በፅኑ እናምናለን” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም የፐሮፌሰር ማዕረግን ግድያ ያነሳሱት ፖስቶች ልጃቸው ሪፖርት ካደረገ በኋላ ለሳምንታት ከፌስቡክ ሳይነሱ የቆዩ ሲሆን አንደኛው ፖስት ከአንድ አመት በላይ ቆይቷል፡፡

ክሱ በስፋት የታዩ ፖስቶችን በሚያበረታታ የፌስቡክ አልጎሪዝም እና የሁከት ቅስቀሳ ተግባራት መካከል ያለውን ግንኙነት ያሳያል።

“በሚያሳዝን ሁኔታ ፖስቶቹ ግጭት ቀስቃሽ ወይ አስደንጋጭ ሲሆኑ ሰዎች በፖስቶቹ ስር ሃሳብ ያሰፍራሉ፣ እነዲሁም ለሌሎች ያጋራሉ፡፡ ይህ ድርጊት ደግሞ የፌስቡክ አልጎሪዝም ፖስቱን ብዙ ሰዉ ጋር እንዲደርስ ያደርገዋል። በዚህ መሰረት የጥላቻ እና ግጭት ቀስቃሽ ፖስቶችን በስፋት እንዲታዩ ያደረጋል፡፡ ለዚህም ነው ፌስቡክ ገዳይ ዲዛይን ነው የምንለው” ትላለች ሮዛ፡፡

ከከሳሾቹ ጋር በመሆን አብረሃም ፌስቡክ የጥላቻ ፖስቶችል በስፋት እንዲታዩ የሚያደርገውን አልጎሪዚም እንዲቀይር ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥ ይሻል፡፡ በተጨማሪም በቂ የይዘት ገምጋሚዎችን መቅጠር፤ ለፕሮፌሰሩ ሞት ይቅርታ እንዲጠይቅ እንዲሁም በፌስቡክ አማካኝነት የጥላቻ እና አመጽ ሰለባ ለሆኑ በፍርድ ቤቱ የተገመገመ 2.4 ቢሊዮን ዶላር ማቋቋሚያ ፈንድ  እንዲከፍል ተይቋል፡፡

ፕሮፌሰር ማዕረግ  ማን ነበሩ ግድያውስ እንዴት ተፈፀመ ?

ለአዲስ ስታንዳርድ መፅሔት በአብረሃም ማዕረግ @AmareMeareg

ፕሮፌሰር ማዕረግ አማረ ከአክሱም ከተማ በ10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አዲ ፀኃፊ፣ለቶ መንደር ውስጥ እአአ መጋቢት 21 1961 ዓ.ም ተወለደ፡፡ ፕሮፌሰር ማዕረግ ለቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ነው፡፡ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአክሱም ከተማ የተከታተለ ሲሆን በ1982 ከሀረመያ የግብርና ኮሌጅ በኬምስትሪ ዲፕሎማ አግኝቷል፡፡ ቀጥለውም በዳባት ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት አግልግሏል፡፡ በ1983 በደርግ መንግስት ታስሮ እስከ ጥር 1985 ድረስ በጎንደር ባእታ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ቆይቷል፡፡

ከእስር ከወጣ በኋላ አማራ ክልል ባሉ በተለያዩ ትምህርት ቤት ውስጥ የማስተማር ስራውን ቀጠለ፡፡ በ1990 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኬሚስትሪ የመጀመሪያ ዲግሪዉን ለማግኘት ትምህርቱ ላይ ተጨማሪ ጥናት አድርጓል። በመቀጠልም ለሶስት አመታት በአማራ ክልል የመምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እንዲሁም በክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ ደረጃ ኤክስፐርት ሆኖ አግልግሏል፡፡

መማር ያላቆመዉ ፐሮፌሰር ማዕረግ አ.አ.አ በ2004 ሁለተኛ ዲግሪውን በአናሊቲካል ኬሜስትሪ እንዲሁም በ2013 ዶክትሬቱን በፊዚካል ኬምስትሪ አግኝቷል፡፡ በዚህ መኋል ነሃሴ 2005 በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የማስተማር እና የምርምር ስራውን ጀምሮም ነበር፡፡

ፐሮፌሰሩ ከሚወደዉ የመምህርነት ሙያ በጊዜ መልቀቅ ስላልፈለገ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለአምስት አመት ለመቆየት ቢወስንም ጥቅምት 29 2021 ዓ.ም የውጭ ጫናን ጨምሮ በኢሜል እና በመልዕክት ይደርሰው በነበረው ማስፈራሪያ ጡረታ ለመጠየቅ ተገዷል፡፡

በአሰቃቂ ሁኔታ እንከተገደለበት ድረስ አባታችን ለዩኒቨርሲቲው በምርምር እና በማስተማር ሙያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን ተገንዝበናል፡፡በ1990ዎቹ እና 2000ሺ ከሰባተኛ አስከ አስረኛ ክፍል የመማሪያ መፅሐፍትን ፅፏል እንዲሁም የአስራ አንደኛ እና አስራ ሁለተኛ ክፍል የመማሪያ መፅሐፍትን የአርትዖት ስራን ሰርቷል፡፡

ከኬሚስትሪ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሃያ ስምንት ጥናቶችን እና የላብራቶሪ ግኝቶችን እና ሪፖርቶችን ይፋ አድርጓል። ከግድያው በኋላ ከታተሙት ስድስት ሳይንሳዊ ስራዎች በተጨማሪ ከ46 በላይ ሳይንሳዊ ፅሑፎችን እንደ ዋና እና ተባባሪ ተመራማሪ አሳትሟል፣ በስድስት ፕሮጀክቶች ላይ ተሳትፏል።

ባደረገዉ አስተዋፅኦም በ2017 ወደ ተባባሪ ፕሮፈሰርነት እድገት የተሰጠው ሲሆን በ2021 በተሰጠው እድገትም በኢትዮጵያ ካሉ ሶስት በአናሊቲካል ክምስትሪ ሙሉ ፐሮፌሰር ካላቸው አንዱ አንዲሆን እንዲሁም በበህርዳር ዩኒቨርሲቲ የአናሊቲካል ኬምስትሪ ብቸኛው አድርጎታል፡፡

መጋቢት 29 ቀን 2021 ዓ/ም ጡረታ ቢወጡም ከዩኒቨርስቲው ጋር በነበረው ስምምነት ለአንድ አመት ያክል ስራውን ቀጥሎበታል። ነሐሴ አርብ 20 ቀን 2021 ዓ/ም ስድስት የታጠቁ የፖሊስ ሃይሎች የክልሉ ፖሊስ ምልክት ያላት ተሽከርካሪ በመያዝ ቤቱንና ወደ ስራ ቦታው ሄደው ያጡት ሲሆን እሱ ግን በተመሳሳይ ቀን ዘመዶቹን ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ ነበር።

ከ50ሺ በላይ ተከታዮች ባለው “BDU STAFF” በሚል የፌስቡክ ገጽ ላይ ጥቅምት 9 እና 10 አባታችን የህወሓት አባል እንደሆነ በመግለፅ  የስም ማጥፋት ዘመቻና የግድያ ዛቻዎችን ተለጥፎ ነበር። በእሱ ላይ ባነጣጠረው የግድያ ዛቻ የቤተሰቦቹን ምክር ወደ ጎን በመተው እሁድ መስከረም 10 ቀን 2021 ዓ/ም ወደ ባህርዳር ተመለሰ። በእለቱ ወደ ባህር ዳር ልዩ ዞን ፖሊስና ጸጥታ ጽህፈት ቤት በአካል በመሄድ እንዲሁም በማግስቱ ሰኞ ጥቅምት ወደ አማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እየፈለጉት እንደሆነ ወይም በህግ ይፈለግ እንደሆነ ጠይቋል። በምላሹም እርሱን እንዳልፈለጉት መልሰውለታል፡፡

በህዳር 3 2021 በመኖሪያ ቤቱ ፊትለፊት በእኩለ ቀን በጥይት ተመቶ ተገደለ፡፡ አባታችን በዛ ቀን ለጡረታ ጉዳይ አንዳንድ ዶክመንቶችን ለማዘጋጀት ወደ ዩኒቨርሲቲው አምርቶ የነበር ሲሆን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ግድያው በመንግስት እና በመንግስታዊ ባልሆኑ አካላት መቀነባበሩን ቤተሰቡ ተረድቷል።

የተወሰኑት አባላት በቤቱ ዙሪያ ለሰዓታት ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን ሌሎች ሦስት አባላት ደግሞ ከመሀል ከተማ አንስቶ እስከ  ቤቱ በሞተር ሳይክል እየተከተሉት ነበር። አባታችን መኪናውን ከግቢው ውጭ አቁሞ በግራ በኩል ያለዉን ዋናውን በር በመክፈት ላይ ሳለ ነበር፣ የአማራ ልዩ ሃይል የደምብ ልብስ የለበሱ ሶስት ታጣቂዎች ሁለት ጠይት ወደ ሰማይ፤ ሰምት ጥይት  በቤቱ አጥር፣ በር እና ክፍሎች ላይ መተኮስ ጀመሩት።

ከገዳዮቹ አንዱ ማስክ ያደረገ ሲሆን ወደ እርሱ በመቅረብ ሁለት ጥይቶችን ተኩሶ የመጀመሪያው ጥይት የአባታችንን ቀኝ እግሩን መታው፡፡ በመቀጠል የተተኮሰው ጥይት በቀኝ ደረቱ ላይ አርፋ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጋለች፡፡

አደጋውን በመጋፈጥ ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ጥረት ያደረጉ ጥቂት ሰዎች በሚያሳዝን ሁኔታ በታጣቁ ሰዎች ተከልክለዋል፡፡ ሰዎቹ የመጀመሪያ ዕርዳታ ለመስጠት እንዲሁም አስክሬኑን ለመሸፈን ተከልክለዋል፡፡

ስስቱ ገዳዮች በ2013 ከልጆቹ በስጦታ የተሰጣቸውን ያሪስ መኪና (80771 AA 2) በፍጥነት ወስደው ከስፍረው ተሰወሩ። አስክሬኑን ሰው እንዲያነሳው ባለመፈቀዱ የማዘጋጃ ቤቱ ሰዎች መጥተው እስኪቀብሩት ድረስ ለሰባት ሰአታት ያህል መሬት ላይ ነበር፡፡

ሀዘናችንን የበለጠ ያከበደብን እሱን ለመቅበር መከልከላችን እና ባህር ዳር ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ሪፖርት እከሚያወጣ ድረስ፣ የቀብሩን ሂደት እና የተቀበረበትን ሳናውቅ መቆየታችን ነው፡፡

የካቲት 23 ቀን 2022 ዓ/ም ይፋ የተደረገው በባለ ሶስት ገጽ ሪፖርት ኮሙሽኑ በአባታችን ላይ ምን አንደተፈጸመ ለመግለጽ ሞክሮ ነበር። ህዳር 3 ቀን 2021 ዓ/ም ጥዋት 4፡00 ላይ ፕሮፌሰር ማዓርግ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ወደ ቤታቸው ተመልሶ ነበር። ከመገደላቸው በፊትም “ማንነታቸው ያልታወቁ” ታጣቂዎች በመኪና ሲከታተሉት ነበር፤ ፖሊስ ከታጣቂዎች ተጨማሪ ግጭት ላለማስነሳት በመፍራት በግዜው ምንም ነገር አላደረገም ሲል ሪፖርቱ ሀትቷል።  

ሪፖርቱ እንደሚለው ግድያው ከተፈፀመ ከበርካት ሰዓታት በኋላ 5 ሰዓት አካባቢ አስክሬኑ ከመኖሪያ ቤታችን 200 ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ፈለገ ህይወት ሪፌራል ሆስፒታል ተወሰደ፡፡ በኋላም ባልታወቀ ቀን የከተማው አስተዳደር አስከሬኑን ወደ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ወስዶ ያለ መቀበሪያ ሣጥን ቀበረው።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.