አዲስ አበባ ጥር 06/2014: የጡት ካንሰር በአለም ዙርያ ተስፋፍተው ከሚገኙት የካንሰር አይነቶች ከቀዳሚው ተርታ ይሰለፋል። እንደ የአለም ጤና ድርጅት በጎርጎሮሳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 2020 ብቻ ከ 2.3 ሚሊዩን በላይ ሴቶች በአለም ላይ የጡት ካንሰር ህክምና ሲያድርጉ ከ685,000 በላይ ሞት ተመዝግቧል በተመሳሳይ አመት። የአለምን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በኢትዮጵያም ያለው የጡት ካንሰር ከፍተኛ ነው። ከጠቅላላው የካንሰር ህመም አይነቶች 32 ከመቶ ሲይዝ በአመት ከ20,000 በላይ ሰዋች ህክምና ያደርጋሉ።
ዶ/ር እንዳለ አንበርብር በጥቁር አንበሳ እሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጡት ካንሰር ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ናቸው። እንደ እሳቸው ገለፃ በትክክል የጡት ካንሰር መንስኤ ይሄ ነው ማለት ባይቻልም አጋላጭ ምክንያቶች ግን አሉት ምሳሌ ሲጋራ ማጨስ፥ አልኮል መጠጣት እና ከልክ ያለፈ ውፍረት ይጠቀሳሉ። ” እንደ ሌሎቹ የካንሰር አይነቶች ያለ ፈዋሽ የሆነ ህክምና የጡት ካንሰር የለውም ነገርግን ልየታ እና አስቀድሞ መመርመር ህክምናው በመጀመሪያዎቹ ደረጃ ላይ እያለ ለመስጠት ያገለግላል።” እንደ ዶክተሩ ገለፃ በበለፀጉ ሀገራት ማሞግራፊ (የጡት ራጅ) የጡት ካንሰር ህመምተኞችን ለመለየት ተግባራዊ ይደረጋል ነገር ግን እንደ ኢትዩጵያ ላሉ ደሀ ሀገሮች ይህ አይነቱ ቅደመ ምርመራ ውድ እና አዋጭ ያልሆነ ነው። ዶ/ር ጨምረውም በራሳቸው የጡት ካንሰር ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ የማይችሉ ሴቶች በወር አንዴ በአቅራቢያቸው ባለ የጤና ተቋም ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ።
የግንዛቤ ማነስ፥ የሰዋች ባህላዊ ህክምናን ማስቀደም እና የካንሰሩ ደረጃ መጨረሻ ሲደርስ ወደ ዘመናዊ ህክምና መምጣት፥ ያኗኗር ዘይቤ ለውጦች እና ከእድሜ መጨመር ጋር የሚፈጠሩ ችግሮች በሀገሪቱ ያለውን የጡት ካንሰር ህክምና እያባባሰ እንደሆነ ያስረዳሉ። እንደ ዶ/ሩ ማብራርያ የካንሰሩ ሁኔታ በሰውነታቸው ከተሰራጨ በኋላ ወደ ህክምና መምጣት በህክምና ወቅት የሚያጋጥም ዋነኛው ተግዳሮት ነው። ” ካንሰሩ ተስፋፍቶ የመጨረሻ ደረጃ ሲደርስ ወደ ህክምና መምጣታቸዉ ህክምናውን በጣም አሰቸጋሪ እና ውጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል ፤ ተያይዞም ብዙዋቹ የጤና ተቋማት መሰረታዊ የሆነ የካንሰር ህክምና አገልግሎት መስጠት አለመቻላቸው ችግሩን ያወሳስበዋል”። ዶክተር እንዳለ ሲቀጥሉም ” አንዴ ወደ ህክምና ቦታ ከመጡ በኋላ የህክምና ወረፍቸው እስኪደረስ ብዙ ይጠብቃሉ ባለው የህክምና መስጪያ እጥረት ምክንያት ይህም የበሽታው ደረጃ እንዲጨምር የራሱ አስተዋፆ አለው ። ይሄ ችግር እኔ በምሰራበት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታም አለ።”
ዶክተር እንዳለ ለአዲስ እስታንዳርድ በእቅድ ተይዞ ወደ ስራ ሊገባ የታሰበውን ሁሉን በአንድ የጡት ካንሰር ማእከል ሲያብራሩ ማእከሉ የጡት ራጅ፥ የቀዶ ጥገና ፥ የጨረር ህክምና እና ቅደመ ምረመራን ጨምሮ ሊያደርግ የሚችል ነው። ጀርመን ሀገር በሚገኘው ማርቲን ሉተርኪንግ ኮሌጅ እርዳታ እየተገነባ ያለው ተቋም የ ቅድመ ልየታ አገልግሎትን ከ ሶስት ወር በፊት ጀምሯል። ቅድመ ልየታው ለካንሰር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና የቤተሰብ የካንሰር ችግር ለነበረባቸው ሰዋች ቅድሚያ ተሰጥቶ መሰራት እንደሚገባው ዶክተሩ አበክረው ገልፀዋል።
ሜሮን ከበደ የደረጃ ሶስት ጡት ካንሰር ታካሚ በቅድመ ልየታው ላይ በዶክተር እንዳለ ሀሳብ ትስማማለች። የ ፒንክ ሎተስ የጡት ካንሰር መረዳጃ ቡድን መስራች የሆነቸው ሜሮን ስታብራራ “ይህንን መረዳጃ ያቋቋምኩት እንደ እኔ በካንሰር ህክምና ውስጥ ያለፉትን ለመርዳት ነው ። አሁን ላይ ግንዛቤ የመስጠት ስራዋችን ጨምረን እየሰራን እንገኛለን በተለይም አሰቀድሞ ምርመራዋችን ማድረግ ላይ ።”
እንደ ሜሮን ገለፃ ባለው የኮሮና ቫይረስ ቅድመ ጥንቃቄ መመሪያዎች ምክንያት በአካል መገናኘት ባይችሉም በማህበራዊ ድህረገፆች ዩትዩብን ጨምሮ ከአባላቶቻቸው እና ደጋፊያቸው ከሆኑት የህክምና ባለሙያዎች ጋር መረጃዎችን ሲለዋወጡ እና ጥያቄዎችን በመመለስ ላይ እየሰሩ ይገኛሉ። በተለይም ቴሌግራም በተባለው የማህበራዊ ድህረገፅ አድራሻቸው ከ800 በላይ አባላት እንዳሏቸው ጨምረው ለአዲስ እስታንዳርድ ነግረዋል።
መረዳጃ ቡድኑ በካንሰር ህክምና ጉንዩሽ ጉዳቶች ላይ እና ለጨረር ህክምና የሚያሰፈልጉ የአኗኗር ዘይቤ ምን አይነት መሆን አለበት የሚለውን ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል። በቀጣይም የመረዳጃ ቡድኑን ወደ ፋውንዴሽን ማሳደግ ፍላጎቷ እንደሆነ ሜሮን አስረድታለች። “ከ አዲስ አበባ ውጭ የሚመጡ የጡት ካንሰር ታካሚዋች በመንግስት ሆስፒታል ወረፋቸው ደርሶ እሰኪታከሙ ድረስ ካንሰሩ ሊስፍፍ ብሎም ከነበረበት ደረጃ ወደ ሌላ ከፍ ይላል ይህንን ክፍተት ለሙላት ገንዘብ ከለጋሾች በማሰባሰብ በግል ጤና ማእከላት ህክምና እንዲያገኙ እንቅስቃሴዋችን እናደርጋለን።”
የጡት ካንሰር ህክምና ተደራሽነትን በተመለከተ ሜሮን አሁንም ከመንግስት ብዙ ነገር ይጠበቃል ብለዋል። ” መንግስት የጨረር ህክምናው በነፃ እንዲያደርገው እንፈልጋለን በተለይም ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በጣም ነው የሚቸገሩት። ተያዬዞም የጡት ካንሰር ህክምና እና ለህክምናው የሚያስፈልጉ ማሽነሪዋች በቀላሉ መገኘት አለባቸው።” ሌላው ሜሮን ያነሱት የካንሰር ህክምና ክፍልን በሰው ሀይል ማደራጀትን አሰፈላጊነት ነው። በመጨረሻም ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የጡት ካንሰር ህክምናን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በሆነ መልኩ እንዲሰሩ አሳስበዋል። አስ