ትንታኔ፡ ለዓመታት መገናኛ መንገዶች የተዘጋባቸው የትግራይ ተወላጆች በመቐለ ከተማ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ሲገናኙ የተለያዩ ስሜቶችን እንጸባርቀዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20/ 2015 ዓ.ም፡- ደማቅ ሰላምት፤ በስሜት መተቃቀፍ፤ መሳሳም፤ እንባና ሳቅ እንዲሁም ጸሎት የዕለቱ ትእይንት ነበሩ። የኢትዮጵያ እየር መንገድ አውሮፕላን ከሁለት እመታት ብኋላ ለመጀመርያ ግዜ ትላንት ረብዕ ታህሳስ 19 ፣ 2015 ዓ/ም  ከአዲስ እበባ ተነስቶ መቐለ ሲያርፍ በመንገደኞቹ ላይ አነዚህ ስሜቶች ይታይባቸው ነበር። የመጀመርያው በረራ በትላንትናው እለት ከስዓት በኋላ በአሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ያረፈ ሲሆን “በዓለም ላይ እጅግ አስከፊው ጦርነት” ከተካሄደ በኋላ እንዳንድ መንገደኞች ለመጀመርያ ግዜ በትውልድ እገራቸው ሲያርፉ መሬቱን ሲሳለሙ ታይተዋል። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮሙዩኒኬሽን ዲፓርትመንት ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፀው በአውሮፕላኑ ውስጥ ከተሳፈሩት መንገደኞች መካከል አብዛኞቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት በመጓዝ ላይ የነበሩ ናቸው። 

አየር መንገዱ ወደ መቐለ ለመብረር ያቀደው የመጀመርያው አውሮፕላን፣ ቦምባርዲየር ኪው 400 (Bombardier Q400) የተባለው ሲሆን አውሮፕላኑ 77 መንገደኞችን ብቻ የመያዝ አቅም ያለው ነበር። ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ፣ ከደንበኞች ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ከ138 በላይ ተሳፋሪዎችን የመጫን አቅም ወዳለው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ሊሻሻል ችሏል።

“በአሁኑ ወቅት ቦምባርዲየር ኪው 400 አውሮፕላኖችን ስራ ላይ በማዋል ከእዲስ እበባ መቐለ የጀመርነው በቀን እንድ በረራ ትኬቶቹ በፍጥነት እየተሸጡ ይገኛሉ፤ ፍላጎተችን በመገንዘብ የበረራ ቁጥር እንጨምራለን” ሲሉ የኮምንኬሽን ዲፓርትመንት ገልጧል። 

ከማክሰኞ ጀምሮ ለተስተዋለው የዋጋ ጭማሪ ምላሽ የሰጠው የኮሙዩኒኬሽን ዲፓርትመንቱ ከአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ባህል ጋር የተጣጣመ ነው ይላሉ “ሁሉም ትኬቶች በተመሳሳይ ዋጋ እይሽጡም፤ ትኬቶችን በተቻለ ፍጥነት የሚገዙ መንገደኞች ርካሹን የታሪፍ ዋጋ የማግኘት እድል እላቸው፤ ትኬቶችን ቆይቶ የሚገዙ መንገደኞች ግን ቀደም ከገዙ መንገደኞች በተጨማሪ ዋጋ  ትኬቱን ያገኛሉ” ብለዋል። 

ይህ ፈጣን እርምጃ ምን ያህል ፍላጎት እንዳለ ማሳያ ነው መሆኑ፤ ላለፉት ሁለት እመታት ከህዳር 19 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ/ም ባለው ግዜ ውስጥ የፌደራል መንግስት ትግራይ ክልል በጊዜያዊ እስተዳደረ እንድትመራ ባደረገው  ግዚያት ውጭ የትግራይ ክልል የመብራት፤ የእየርና ምድር ትራንስፖርት፤ የቴሌኮምና ባንክ አገልግሎቶች ተቋርጠው የቆየ ሲሆን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እነዚህን መሰረታዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ያቀረቡት አቤቱታ የኢትዮጵያን አስከፊ ጦርነት ለመፍታት የተደረገው ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ አካል ነበር።

ዛሬ (ሐሙስ) ታህሳስ 20 2015ዓ/ም ከእዲስ እበባ መቐለ በረራ ለማድረግ ትኬት የቆረጠችው፣ ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች 28 አመቷ ወጣት፣  ለመሄጃ ብቻ 4650 ብር የከፈለች ሲሆን “በመቐለና በሌላ አካባቢ የሚገኙ ቤተሰቦቼን ለማግኝት በጣም ጓጉቻለሁ” ስትል ለአዲስ ስታንዳርድ ሃሳብዋን ተናግራለች።

ከድሰታዋ በተጨማሪ ውስጧ በፍርሃት ተሞልቷል “በመቐለ ከተማ ውስጥ በስኳር ህምም የምትሰቃይ የሁለት እመት ታናሽ እህት እለችኝ፤ እሁን ትልቁ ስጋቴ ህይወት ትኖራለች ወይስ እትኖርም የሚለውን ነው” ስትል ስሜቷን እጋርታለች። 

ክፍለ ሓጎስ ሌላኛው ከፍቅር እጋሩ ጋር ለመገናኘት የሚጓዝ  መንገደኛ ነው። ሚስቱ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ለማስመጣት በእየር መንገዱ ኦንላይን መተግበሪያ  ወንበር ለማስያዝ የሞከረ ሲሆን ተሳፋሪ በመብዛቱ ለፈለገው ቀን ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ ክፍለ “የኢትዮጵያ እየር መንገድ የበረራውን ቁጥር መጨመር እለበት” ሲል ሃሳቡን ለእዲስ ስታንዳርድ እጋርተዋል። 

የኢትዮጵያውያን እናቶች እንዱ ባህል የሆነው፤ ሁለት ሴት ልጆቻቸውን ለማዋለድ በክረምት 2013 ዓ/ም ወደ እዲስ አበባ የመጡት እማማ ንግስቲ ትግራይ ቴሌቭዥን እቅርቧቸው ነበር። እማማ ንግስቲ የ52 ዕድሜ ባለፈጸጋ የሆኑ ባለቤታቸውን እንዲሁም ከመላ የቤተሰብ አባላቸው ተለይተው ሁለት አመታትን ሊያሳልፉ ተገደዋል፡፡ የመገናኛ መንገዶች ስላልነበር እማማ ንግስቲ ወደ ቤት እየሄዱ መሆኑን ማንም እያቅም ነበር።  የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአልን ምክንያት በማድረግ ቤተሰቡ በአንድነት ተሰባስቦ እያለ ነው የመጡት፡፡  ከቤተሰብ ጋር ሲገናኙም እጅግ ስሜት የተሞላበት ነበር። 

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ በመቐለ ድንገተኛ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ልዑካን ቡድኑ ከክልሉ ባለስልጣና ከደብረዮን ገ/ሚካኤል ጋር ውይይት እስካደረጉበት ድረስ፣ ከሶስት ቀናት በፊት እነዚህ ታሪኮች ያልታሰቡ ነበሩ።  

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ በረራዎ እንደገና መጀመሩ ሁለቱ ወገኖች በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈራረሙት ዘላቂ ጦርነት የማቆም ስምምነት (CoHA) እንዱ አካል ነው፡፡

አየር መንገድ እንቅስቃሴውን ለማስቀጠል በማሰብ ማንኛውም ሰው ለአገር ውስጥ ጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ይዞ የሚመጣ ማንኛውም ሰው ለበረራ ብቁ እንደሆነ እና የደህንነት ፍተሻዎች ዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት እንደሚከናወኑ ገልጧል።

ኢትዮ ቴሌኮም በመቐለ የኮሙዩኒኬሽን ሙከራ መጀመሩን ረቡዕ እለት ያስታወሰ ሲሆን  የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን በትግራይ ክልል ለሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ለማጓጓዝ እና ለማከፋፈል 14 የነዳጅ ማከፋፈያ ኩባንያዎች ከጅቡቲ ወደብ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል እንዲያጓጉዙ ፍቃድ ስጥቷል፤ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት 14 ነዳጅ አከፋፋዮች አገልግሎት ይሰጡ  እንደነበር ባለሥልጣኑ ተናግሯል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.