ሰበር ፡- በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የኢትጵያ የሰላም ድርድር ግጭት ማቆም ስምምነት ለይ ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 24 2015 ዓ.ም፡- በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረውን አውዳሚ ጦርነት ለማስቆም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በደቡብ አፍሪካ በሚካሔደው የሰላም ድርድር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን አሳወቁ፡፡

የሰላም ድርድሩ በፌዴራል መንግስት ተወካዮች እና በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መሃል በአፍሪካ ህብረት መሪነት በዝግና በከፍተኛ ምስጥራዊነት ከማክሰኞ ጥቅምት 25 ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

እሁድ ጥቅምት 20 ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበው ድርድር እስከ ዛሬ የቀጠለ ሲሆን የድርድሩን ውጤት በተመለከተ ይህ የመጀመሪያው ኦፊሴላዊ መረጃ ነዉ::

የተኩስ አቁም ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እና በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አንዲሁም የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ ንጉካ ከሚምሩት የሰላም ንግግር የሚጠበቅ ዉጤት ነበር።

የስምምነቱ ሙሉ ዝርዝር ጉዳይ ገና ያልተገለፀ ቢሆንም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት “አፋጣኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እንዲሁም የሰብዓዊ አገልግሎት ዳግም እንዲጀመር” በድርድሩ ከስምምነት አንዲደረስ ጥቅምት 5 ቀን ጥሪ አቅርበዋል

አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋ አምባሳደር ማይክ ሀመር በደቡብ አፍሪካ “እንደ ተሳታፊ እና ታዛቢ ሆነው በቀጠሉበት” የሰላም ንግግር “ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ ችግር ውስጥ ላሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ፣ ሲቪሎችን ለመጠበቅ እርምጃዎችን ማረጋገጥ እና የኤርትራን ከሰሜን ኢትዮጵያ መውጣት” ዉጤቶች አንደምትጠብቅ ስታሳስብ ቆይታለች::

የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት እስካሁን ስለስምምነቱ ያሉት ነገር የለም::

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሲጂቲኤን (CGTN) ጋር ባደረጉት ቆይታ የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልል ባለስልጣናት “የሀገሪቱን ህግ እና ህገ መንግስቱን እንዲያከብሩና እንደ አንድ የኢትዮጵያ ክልል እንዲሆኑ” ለማሳመን እየሞከረ ነው ብለው ነበር:: አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.