ዜና፡ በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት የኢትዮጵያን መንግስት ትብብር በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17/2015 ዓ.ም፡- በሱዳን የተፈጠረው ቀውስ አሁንም አልበረደም። የኢድ አልፈጥር በአልን ተንተርሶ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ባይተገበርም የተወሰነ እፎይታ ያገኙ አከባቢዎች መኖራቸውን በርካታ መገናኛ ብዙሃን አመላክተዋል። ይህ የታየው እጅግ ውስን የተኩስ ማቆም ተነሳሽነት ትላንትም ቀጥሎ ሁለቱ ጀነራሎች ለተጨማሪ 72 ሰዓታት ተኩስ