ዜና፡ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ባለሞያወችን ስልጣን እንዲቋረጥ ለማስደረግ ኢትዮጵያ የአሜሪካንን ድጋፍ ጠየቀች
አዲስ አበባ፣ጥር 26/ 2015 ዓ.ም፡– የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ ቡድን በኢትዮጵያ ስልጣን እና ተግባሩ እንዲቋረጥ ኢትዮጵያ የአሜሪካንን ድጋፍ ጠየቀች። ኢትዮጵያ ጥሪውን ያቀረበችው ትላንት የአሜሪካን ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑት አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው ምስጋኑ አረጋ በተወያዩበት ውቅት መሆኑን