ዜና፦ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ በምስራቅ ወለጋ በ15 አማኞች ላይ የተፈፀመውን ግድያ አወገዘች፤ በመንግስት ላይም ቅሬታ አቀረበች
አዲስ አበባ፡ህዳር 5/2015 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን በጋሎ ቀበሌ ሙለታ ገላ ቤተክርስቲያን በአማኞች ላይ የተፈጸመውን ኢ-ሰብአዊ ግድያ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነየሱስ አወገዘች። ከቤተክሪስትያኗ ባለፈው ሳምንት ዐርብ ህዳር 02፣ 2015 በወጣዉ መግለጫ እንደተመለከተው በ15 አማኞቿ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በማውገዝ ለሟች ቤተሰቦች እና ለቤተክርስቲያኑ