ዜና፡-ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ከህውሀት ታጣቂዎች ነፃ ወጡ

አዲስ አበባ ፣ ኅዳር 28/2014-ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ አማራ እና አፋር ልዩ ሃይል እንዲሁም  (ፋኖ) ሚሊሻዎች በጋራ  ህዳር 20/3/2014 በአማራ ክልል የሚገኙ ደሴን እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ከትግራይ ኃይሎች መልሰው ወስደዋል።

እንደ መንግስት ኮሚኒኬሽን ገለፃ ከሁለቱ ከተሞች በተጨማሪ ምስራቅ ግንባር ላይ የሚገኘው ባቲን፣ ቀርሳን፣ ገርባን እና ደጋንን   ሙሉ ለሙሉ ነፃ የወጡ ሲሆን በሐርቡ ግንባር ደግሞ ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሸዋሮቢት፣ በጀውሀ፣ በሰንበቴ፣ በአጣዬና ካራቆሬ ከተሞች የሚያልፈውን የከፍተኛ መስመር በመጠገን ለስርጭት መስመሮች ኃይል መስጠት እንዲችሉ ዝግጁ የማድረግ ሥራ አጠናቋል።በተጨማሪም እንደ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል  በቀጣዮቹ ቀናት ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው መስመር የመጠገን ሥራ የሚሰራ መሆኑን ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል።አ.ስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.