ዜና፡-የተራራ ኔትዎርክ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ አርብ ጠዋት በፖሊስ ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዶ ታሰረ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 1/2014-ጋዜጠኛ ታምራት ከመኖሪያ ቤቱ አርብ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ገደማ ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል ነው ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰደው እና

የጋዜጠኛውን የመኖሪያ ቤትእና ቢሮ በመፈተሽም ለመረጃ ይፈለጋሉ ያሏቸውን የሚዲያ ዕቃዎች በሙሉ በዋናነት፣ ላፕቶፕ ፣ኮምፒተሮች፣ መቅረፀ ድምፅ፣ ፋላሽ ሚሞሪ፣ እና ሌሎች የሚዲያ መገልገያ መሣሪያዎች በፖሊስ መወሰዳውን  አርብ ለት ተራራ ሚዲያ በፌስ ቡክ ገልፁ ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛ ታምራትን ለጥያቄ እንፈልግሀለን ብለው አርብ ጠዋት 4፡ 30 ላይ ከመኖሪያ ቤቱ እንደወሰዱት ለአዲስ ስታንዳርድ የተናገረችው ሚስቱ ሰላም በላይ ” በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 3ተኛ  ፖሊስ ጣቢያ ነው የታሰረው ” ያለችው ሰላም ለጥያቄ እንፈልገዋለን ከማለት ውጪ ፖሊስ ለምን እንደሚያስረው የነገረን ነገር የለም ብላለች፡፡ የፌራል ፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑት ኮማንደር ጀይላን አብዲን ጋዜጠኛ ታምራት በምን ምክንያት እንደታሰረ ከአዲስ እስታንዳርድ ለቀረበላቸው ጥያቄ አዲስ አበባ ፖሊስ እንድንጠይቅ ምላሽ ሰተዋል ፡፡ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፋቱ ጋር ምላሽ ለማግኘት  በተደጋጋ  በስልክ ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም፡፡አ.ስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.