አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2015 ዓ.ም፡- በትላንትናው ዕለት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ ታጥቆ ለሚብቀሳቀሰው የኦነግ ሸኔ ቡድን የሰላም እና የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የሰላም እና የዕርቅ ጥያቄውን እንደሚቀበለው አስታውቋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥባቸው የሚፈልጋቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በዝርዘር አቅርቧል።
የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን ሁለተኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአዳማ ከተማ ገልመ አባገዳ በማካሄድ ላይ ሲሆን የክልሉ ፕሬዚዳንት ለጨፌው ባቀረቡት የስድስት ወራት የስራ አስፈፃሚ ሪፖርት በክልሉ የትጥቅ ትግል በማድረግ የሚንቀሳቀሰው ኦነግ ሸኔ በእርቅ ወደ ሰላማዊ መንገድ ተመልሶ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል።
የሰላም እና የእርቅ ጥሪውን በማይቀበሉት ላይ ግን የህግ ማስከበር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልጸዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ( መንግስት ሸኔ ብሎ የሚጠራው) ባወጣው መግለጫ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ የተከሰቱ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ በድርድር ይፈታሉ ብሎ እንደሚያምን አስታውቆ ይህንንም ከመጀመሪያው ጀምሮ ሳቀነቅን ነበር፣ በቅርቡ ይፋ ባደረኩት ማኒፌስቶም ላይ ገልጫለሁ ብሏል።
በዋናነት ያቀረበውም መንግስት ጉዳዩን አሳሳቢነት የያዘበት መንገድ ሲሆን የክልሉ የተፈጠረውን ግጭት በማሳነስ በሀገር ውስጥ አደራዳሪዎች ይፈታል ማለቱ ስህተት መሆኑን አስታውቋል። ይህ አካሄድ በፍጹም ተቀባይነት እንደማይኖረው በምክንያት አስደግፎ አመላክቷል። ካቀረባቸው ምክንያቶች ውስጥም ጽንፍ በያዘው የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ገለልተኛ ወገን አደራዳሪ ማግኘት እጅግ አዳጋች መሆኑን ጠቁሞ ቢገኝ እንኳን ከመንግስት የተጽእኖ ወጥመድ ሊያመልጥ አይችልም ሲል ገልጿል።
በተጨማሪ ያቀረበው ምክንያት ትርጉም ያለው ድርድር ለማካሄድ ክህሎት፣ የሎጅስቲክ እና መሰል አቅርቦት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁሞ የድርጅቱ ኮማንደሮች እና ተደራዳሪዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ እና ከቀውሰ ቀጠናው በማናቸው ግዜ እንዲወጡና እንዲገቡ ለማስቻል የጸጥታ እና የትራንስፖርተ አቅርቦት ሊረጋገጥ የሚችለው በአለም አቀፍ አካላት ብቻ ነው ብሏል።
ሂደቱ በገለልተኛ ሶስተኛ አካል ታዛቢ እንደሚያስፈልገው የገለጸው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መግለጫ ይህ ካልሆነ ግን ከዚህ ቀደም በኦነግ እና በመንግስት መካከል በአስመራ እንደተካሄደው ስምምነት ውጤት አይኖረውም ሲል አመላክቷል። የስምምነቶቹን ይዘቶች አከባበር ዙሪያ መተማመን የሚቻለው በአለም አቀፍ ዋስትና ብቻ ነው ያለው ሸኔ ይህም ከማናቸውም በላይ ወሳኝ መሆኑን አስረግጧል።
የኦሮምያ ክልል መንግስት በድርድሩ እንዲሳተፍ የሚፈቀድ ቢሆንም ድርድሩ በዋናነት መካሄድ ያለበት ግድ በፌደራል መንግስቱ እና በኦነግ ሽኔ ማካከል መሆን እንዳለበትም አስታውቋል።
በቴክኒክ ደረጀ የክልሉ መንግስት ያቀረበው የሰላም ጥሪ በቀጥታ ኦነግን አለመሆኑን ያመላከተው መግለጫው በይዘት ደረጃ የሚፈጥረው ልዩነት ባይኖርም የመንግስትን የሰላም አካሄድ ላይ የግልጽነት ጥያቄ እንደሚጭር አትቷል።
በመጨረሻም የፌደራል መንግስቱ የኦሮምያን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመቅረፍ ቁርጠኛ ከሆነ ስርአቱን የተከተለ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ መንገዶችን እንዲጠቀም አሳስቧል። አስ