አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5/ 2015 ዓ.ም – የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መሪዎች በትላንትናው ዕለት ሶስት ጉብኝቶችን አካሂደዋል። ተጠቁሟል። የኤርትራዋ አስመራ ከተማ የሁለት ሀገራት ከፍተኛ ልዑካንን ትላንት ያስተናገደች ሲሆን ጁባ ደግሞ አንድ ጉብኝት አስተናግዳለች። የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጁባ አቅንተው ከሀገሪቱ መሪዎች ጋረ መክረዋል።
ጉብኝቶቹ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ከሚያደርጉት ገብኝት አንድ ቀን ቀድሞ የተካሄደ መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ግርምትን ፈጥሯል። አንቶኒ ብሊንከን በአዲስ አበባ ቆይታቸው በቅርቡ በዋሽንግተን ተካሂዶ በነበረው የዩኤስ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ወቅት የተደረሱ ስምምነቶች ትግበራን ከህብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ ጋር እንደሚወያዩ ተገልጿል።
ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በጁባ የነበራቸውን ቆይታ አስመልክተው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ፌስቡክ እንዳሰፈሩት መልዕክት ከሆነ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን መረጋጋት እና ሰላም ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አጋርተው ተመልሰዋል። የደቡብ ሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ሳልቫ ኪር ከአብይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች በ2018 የተፈረመው የሰላም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ መክረዋል ሲሉ ለጋዜጠኞች በጁባ ተናግረዋል።
ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ታከብራለች ማለታቸውንም መቀመጫውን ጁባ ያደረገው ራድዮታማዙጂ በድረገጹ አስፍሯል። ድረገጹ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋና አረጋ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲጠበቅ በልዩ ትኩረት እንደምትሰራ አስታውቀው ችግሮቿን ሁሉ በሰላማዊ መንገድ እንድትፈታ ለማስቻል ቁርጠኛ መሆናን ገልጸዋል ብሏል። አምባሳደሩ በተጨማሪም ጠ/ሚኒስትር አብይን ባሸበረቀ መንገድ ስለተቀበላችኋቸው እጅግ እናመሰግናል ማለታቸውንም አካቷል።
በትላንትናው ዕለት ሌላኛው በቀጠናው የተካሄደው ጉብኝት የሱዳኑ ከፍተኛ መሪ ጀኔራል መሐመድ ደጋሎ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያካሄዱት ነበር። ጀኔራል መሐመድ ደጋሎ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መክረው መመለሳቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት አስታውቋል።
ሁለቱም መሪዎች በአህጉራዊ እና አለምአቀፍ ጉዳዮች መመከራቸውን ያመላከተው የሱዳን ዜና አገልግሎት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የሱዳንን ጉዳይ በትኩረት እንደሚከታተሉት በመግለጽ ሱዳን የውስጥ ጉዳዮቿን በሰላማዊ መንገድ እንድትፈታ ለማስቻል ሀገራቸው ድጋፏ እንደማይለያት ማስታወቃቸውን አካቷል። ጀነራል ዳጋሎ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ዝርዝር መረጃ ነግረዋቸዋል ሲል ዘገባው አመላክቷል።
ሌላኛው ትላንት የካቲት 4 ቀን 2015 አመሻሽ ላይ የተሰማው ጉብኝ ደግሞ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ማህሙድ በስምት ወራት ውስጥ ወደ አስመራ ያደረጉት ሶስተኛ ጉብኝት ነበር። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት አስመራ የተገኙት ለሁለት ቀናት ጉብኝት መሆኑን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር በድረገጹ አስነብቧል። ሁለቱም መሪዎች የጋራ በሆኑ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ድረገጹ ጠቁሟል። አስ