ዜና: የአፍሪካ ህብረት የፀጥታ ምክር ቤት በኢትዮዽያ ጉዳይ መከረ፣ የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት በበኩሉ ዛሬ ምሽት ላይ በዝግ ይመክራል

የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም፡– የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የኢትዮጵያ የሰላም ሂደት አስመልክቶ  ማብራሪያ ለመስማት  ዛሬ ስብሰባ እያካሄደ ነው።

እንደ አማኒ አፍሪካ የዛሬው ስብሰባ “በመጀመሪያ በካውንስሉ ወርሃዊ የስራ መርሃ ግብር ውስጥ አልተካተተም“፡፡ ሌላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት “ሰላም እና ደኅንነት በአፍሪካ” በሚል መሪ ቃል ሌላ “የግል ስብሰባ” ዛሬ ተካሄዷል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት የመጨረሻ ስብሰባ እ.አ.አ. ነሐሴ 4 ቀን 2022 የተካሄደ ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ጦርነት ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ስላደረጉት እንቅስቃሴ ገለጻ አድርገዋል። የኦባሳንጆ የነሀሴ 1 ቀን የሰጡት አጭር መግለጫ የካቲት 10 ቀን ለካውንስሉ ንግግር ካደረገ በኋላ ነበር፡፡

የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ከሚያደርጉት ስብሰባ ቀደም ብሎ በትናንትናው እለት የአሜሪካ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተው ነበር፡፡

በውይይቱ ወቅት ዋና ጸሃፊ ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት መጠናከር እና የጅምላ ጭፍጨፋ አደጋ እንዳሳሰባቸው ገልፀው ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ ያልተቋረጠ ሰብአዊ አቅርቦት አስፈላጊነትንና በሚቀጥለው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት በሚመራው ውይይት የታማኝነት ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን እና ኤርትራ ጦሯን ከሰሜን ኢትዮጵያ እንድታስወጣ አሳስበዋል።

የዛሬው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በ3 የምክር ቤቱ አባላት ማለትም በጋቦን፣ ጋና እና ኬንያ -በጥቅምት 17 የተጠየቀ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት አፋጣኝ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ጥሪ እና በትግራይ ክልል የሰብአዊ አገልግሎት እንዲቀጥል ጥሪ ካቀርቡ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው። ይህ የተኩስ አቁም ጥሪ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ፍቃድኝነታቸውን የገልፁት ነበር፡፡

ነገር ግን የፌደራል መንግስት ጥቅምት 17 ቀን ባወጣው መግለጫ “የህወሓትን ተደጋጋሚ ጥቃት እና የውጭ ሃይሎች ጋር የሚያደርገውን ትብብር” ለመከላከል የሚወስደውን  እርምጃ” እንደሚቀጥል አስታውቋል። የፌደራል መንግስትም “በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ኤርፖርቶች፣ ሌሎች የፌደራል ተቋማትን በአፋጣኝ መቆጣጠር” አስፈላጊ መሆኑን ገልፆ  የትግራይ ክልላዊ መንግስትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር፤ ሲቪሎች እና የእርዳታ ሰራተኞች የትግራይ ሃይሎች ከሚጠቀሙባቸው ወታደራዊ መሳሪያዎች እንዲርቁ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም  የአማራ ክልል ሀይል በጋራ በመሆን  የትግራይን ሀይል ከትግራይ ክልል ለማፈናቀል ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ በመሆናቸው ጦርነቱ ተባብሷል ተብሏል።  ማክሰኞ  እለት የፌደራሉ መንግስት “በከተሞች ላይ  ጦርነት ሳያደርግ” ሽሬ፣ አላማጣ እና ኮረምን መቆጣጠሩን የገለጸ ሲሆን  በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት  አልደረሰም ብሏል፡፡

ነገር ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዘለዘሌ ከተፈናቀሉት 210,000 አዲስ ተፈናቃዮች መካከል አብዛኞቹ “በድሃ ሁኔታ ውስጥ ናቸው፣ አብዛኞቹ  ለቀዝቃዛ አየር ሁኔታ እና ለሌሎች ጥበቃ ስጋቶች በተጋለጡ አስከፊ ቦታዎች ናቸው” ሲል ገልጿል። ተፈናቃዮቹ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ከዘላዘለ ታህታይ አድያቦ እና ሸራሮ የመጡ ሲቪሎች  ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት “በጣም የሚፈለጉትን ሰብአዊ እርዳታ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ያሉ ሲቪሎች በጥቅምት 14 ቀን በተከፈተ ተኩስ ስር ወድቀዋል፣ ይህም የአካል ጉዳት እና የህይወት መጥፋት አስከትሏል” ብሏል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጥቅምት 17(እ.አ.አ) በሰጡት መግለጫ  በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ “ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” ሲል አስጠንቅቋል።

“ንፁሀን ዜጎችም እጅግ አሰቃቂ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው፣ በትግራይ ያለው ጦርነት በአስቸኳይ መቆም አለበት፣ የኤርትራ የታጠቁ ሃይሎች ከኢትዮጵያ በፍጥነት መውጣት አለባቸው” ብለዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ የጉተሬዝን መግለጫን እውነታውን የማያሳይ “ያልተረጋገጠ”  ሲሉ ተቃውመዋል።

አምባሳደሩ በትዊተር ገፃቸው እንደተናገሩት “ከተመረጡት እና ተገቢ ያልሆነ የተጋነኑ ውንጀላዎች አንዳቸውም እውነታውን አይወክልም” ብለዋል።  አክለውም መግለጫው “በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሰላም ጥረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አወንታዊ እና ገንቢ ሚና የመጫወት አቅምን ያዳክማል” ብሏል።

የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤቶት ዛሬ ያካሄዱት ስብሰባ ሰኞ ጥቅምት 24 በደቡብ አፍሪካ ሊከሄድ  ቀነ ቀጠሮ ከተያዘለት የሰላም ውይይት በፊት ነው፡፡ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ድርድሩ ጥቅምት 24 ቀን 2022 በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ መታቀዱን ገልፆልናል ሲትል ኢትዮጵያ ትናንት ገልጻ እንደምትሳተፍም  አሳዋቃለች። ከትግራይ ባለስልጣናት  በድጋሚ የተቀጠረውን የሰላም ድርድር አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ የለም፡፡ የአፍሪካ ህብረትም በዝርዝሩ ላይ እስካሁን የለው ነገር የለም።

የአህጉሪቱ ድርጅት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሮችን ለማዘጋጀት ያደረገው ሁለተኛው ሙከራ ነው። መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም አፍሪካ ህብረት ለትግራዩ መሪ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በፃፈዉ ዳብዳቤ ጥቅምት 29 2015 ዓ/ም አሁድ በደቡብ አፍሪካ ሊደረግ ታቅዶ በነበረዉ የሰላም ድርድር አንዲሳተፉ መጋበዙ ይታወሳል። ተመሳሳይ ጥሪ ለፈዴራሉ መንግስትም የቀረበ ሲሆን ሁለቱም አካላት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ነበር።

እንደ አማኒ አፍሪካ፤ የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት  የሚካሄደው ስብሰባ ዳግም ያገረሸው ግጭት እና በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት እንዳሳሰበው እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ጥሪያቸውን እና የሰብአዊ አገልግሎቶችን እንዲጀመሩ ያቀረቡትን ጥሪ  ለመቀበል መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.