አዲስ አበባ የካቲት 29 2014 :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቸሌት በ49ኛ ለሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባኤ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ“በአፋር እና አማራ ክልል ግጭት መስፋፋት እና መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ ሪፖርቶችን ማግኘተታቸውንና መቀጠላቸውን” ተናገሩ ።
ህዳር 13 ቀን 2014 እና በየካቲት 21 ቀን 2014 መካከል ያለዉን ጊዜ የሚያካትተው የሃላፊዋ ሪፖርት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እና የጸጥታ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሷል፣ ይህም በአብዛኛው በትግራይ ያለው ግጭት ወደ ሌሎች የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በመስፋፋቱ ነው ሲል ያትታል።
ፅህፈት ቤቱ ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ አየር ሃይል በትግራይ እና በአፋር ባደረገው የአየር ላይ ጥቃት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳትና የዜጎች ንብረት መውደም ምክንያት መሆኑን ገልጾ በአየር ላይ በደረሰ ጥቃት 304 ሰዎች ሲሞቱ 373 ሰዎች አካላዊ ጉዳት ደርሷል ሲል ገልጿል።
በታህሳስ 2014 የኢትዮጵያ አየር ሃይል በአላማጣ ከተማ በሚገኘው ገበያ እና ሆቴል ላይ ባደረገው የአየር ጥቃትን ጨምሮ በትግራይ ክልል 120 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸው እና 145 መቁሰላቸው ተገልጹኣለ። በጥር 2022 የኢትዮጵያ አየር ሃይል በትግራይ ሁለት የአየር ወረራዎች በማይ-አይኒ የስደተኞች ካምፕ እና በደደቢት የተፈናቀሉ ዜጎች ካምፕ ላይ ባደረገው ጥቃት 60 ሰዎች ሲሞቱ 169 ቆስለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ሃላፊ ሚሼል ባቸሌት ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ ክልል ከሚገኙት አምስት ሰዎች ውስጥ አራቱ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ሲሆን ግማሾቹ ነፍሰ ጡር እና ጡት የሚያጠቡ ሴቶች ደግሞ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አለባቸው ሲል የአለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።አስ