ዜና: በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ በተፈፀመው ግድያ መንግስትን የወቀሱት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢዜማ ፓርቲ መሪ ፣ ፎቶ- ከቪዲዮ የተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28/ 2015 ዓ.ም፡ በኢትዯጵያ የሚገኙ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ የተፈፀመው ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ ጋር በተያያዘ መንግስትን ወቀሰው አሁንም አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁ።

ፓርቲዎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣እናት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የኦሮሞ  ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሲሆኑ በተለያየ ግዜ በምስራቅ ወለጋ በተካሄደው ግድያ የፌደራል እና የክልሉ መንግስታት ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ  አቅርበዋል።

በወንጀሉ የተሳተፉ ኃይሎች  በሙሉ በአስቸኳይ ለሕግ እንዲቀርቡም ፓርሪዎቹ የጠየቁ ሲሆን አጥፊዎች ፍትህ ፊት ቀርበው መጠየቅ ካልቻሉና የህግ የበላይነት ካልተረጋገጠ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም ሊመጣ አይችልም ሲሉ አቋማቸውን አስታውቀዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በሚገኙት ኪረሙ፣ ጊዳ አያና እና ሀሮ አካባቢዎች፤ ዘላቂ ሰላም እስኪሰፍን ድረስ በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደሩ እና የመከላከያ ሰራዊት ስፍራዎቹን እንዲቆጣጠር የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳስበዋል።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው እንዳሰፈሩት በድርጊቱ የተሳተፉ  በሙሉ በአስቸኳይ ለህግ መቅረብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና እናት ፓርቲ ትናት በሰጡት የጋራ መግለጫ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ፣ ጊዳ አያና እና ሀሮ አካባቢዎች ከሰሞኑ “እጅግ የሚሰቀጥጡ ፍጅቶች” መከናወናቸውን እንዳሳዘናቸው ገልፀው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን፣ ሺዎች ከቤት ንብረት መፈናቀላቸውን እና ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት መውደሙን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በበኩሉ  መንግስት የጸጥታ ኃይሎች በቀላሉ መድረስ በማይችሉባቸው አካባቢዎች ያሉ ማህበረሰቦችን እንዲያስታጥቅ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን መንግስት ከችግር ጋር በተያያዘ የወሰደው እርምጃ ካለ፤ ለህዝብ እንዲያሳውቅም ፓርቲው ጠይቋል።

ኢዜማ  በመግለጫው የኦሮሚያ ክልል እና የፌደራል መንግስት  የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ እና የህግ የበላይነት ማስከበር አልቻሉም የሚል ወቀሳን ሰንዝሯል። ”የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት በማስጠበቅ ንጹሃን ላይ የሚደርስን ግፍ ያስቆማል ተብሎ የሚታሰብ የጸጥታ ኃይል፤ ከግፈኞች ጎን በመቆም የማፈናቀል እና የግድያዎች አስተባባሪ ሆነው ተመልክተናል” ሲል ኢዜማ ወንጅሏል። 

“የመንግስት የጸጥታ ኃይል በቀላሉ መድረስ በማይችልባቸው እና በመደበኛ የጸጥታ ኃይል መጠበቅ አስቸጋሪ በሆኑባቸው አካባቢዎች፤ በህጋዊ አሰራርና በተደራጀ መንገድ ማህበረሰቡን ማስታጠቅ እና ራሱን ከመሰል እልቂት በጽናት እንዲከላከል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን” አስምሮበታል።

ፓርቲው ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በመንግስት ባለስልጣናት ድጋፍ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግፍ እየፈፀመ ነው መንግስትን አሸባሪ ቡድኖችን የሚይዝ እና የሚደግፍ መዋቅር አለው ሲል ክስ ሰንዝሯል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ እነዳስታወቀው በምስራቅ ወለጋ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በብልፅግና ፓርቲ የሰለጠኑና የታጠቁ የፋኖ ሃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈፀሙት ዘግናኝ ጭፍጨፋ አውግዞ ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ራሱን  እንዲከላከል ጥሪ አቅርቧል።

ኦነግ አያይዞም መንግስት በንፁሀን ዜጎች ላይ “ኃላፊነት የጎደለው እና አረመኔያዊ ግድያ” ፈጽሟል ብሎ የከሰሰውን “ፋኖ ሚሊሻ” የተባለውን መደበኛ ያልሆነ የታጠቀ ቡድንን በማስታጠቅና በማሰልጠን ኮንኗል።

ኦነግ ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ የኦሮሞ ህዝብ እራሱን እንዲከላከል ጠይቋል።  “በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በየደረጃው ያሉ መምህራን በገጠር ያሉ ገበሬዎች እና ቄሮዎች እራሳቸውን መከላከል አለባቸው” ሲል በመግለጫው አመልክቷል::

በሳምንቱ መገባደጃ ላይ የፌደራል መንግስትና የክልል የጸጥታ ሃይሎች እና የፋኖ ሚሊሻ ታጣቂ ቡድኖች እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት በሌላ በኩል ግጭት መባባሱን የሚገልጹ በርካታ ውዝግቦች እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሲቪል መንስኤዎች እና  የጅምላ መፈናቀ እንዳለም ጠቁሟል።

አዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው በሁለት ቀናት በ25 እና 29 በደረሰው ጥቃት የኪረሙ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ ዳምጠው ከፍያለው ገመዳን ጨምሮ ሰዎች መገደላቸውንና ከ350 ሺህ በላይ  የኪሬሙ ወረዳ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ዘግቧል

ሁከቱን ተከትሎ ማክሰኞ በበርካታ ከተሞች እና ከተሞች ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ቅጥር ግቢ ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.