አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 10/2015 ዓ.ም፡- በሀገራቸው የተከሰተውነ ጦርነት ሸሸተው ከ75 ሺ በላይ ሱዳናውያን ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመላክታል። አብዘሃኛዎቹ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ሱዳናውያን ሰደተኞች ደግሞ በአማራ ክልል በኩል መሆኑን መረጃዎቹ ያሳያሉ።
ባለፉት ሳምንታት በአማራ ክልል ተከስቶ የነበረው ቀውስ ሱዳናውያኑን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳስጨነቃቸው ዳባንጋ ሱዳን ለተሰኘ የሀገሪቱ ሚዲያ በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል፤ ከሞቀ ቤታቸው ሸሽተው ለስደት የዳረጋቸውን ጦርነት አሁን ደግሞ በስደት ተጠልለው ወደሚገኙበት የአማራ ክልል መምጣቱን በማስታወቅ።
ጦርነትን ሸሽተን ጦርነት ውስጥ ገባን ሲሉ በአማራ ክልል በጎንደር እና በባህርዳር ከተማ የሚኖሩ ሱዳናውያን መናገራቸውን ያስነበበው የዳባንጋ ድረገጽ ከተሞቹን ጥለው ለሶስተኛ ስደት መዳረጋቸውን አስታውቋል፤ ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸውን ጠቁሟል።
በርካታ ሱዳናውያን የአማራ ክልልን ለቀው ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸውን ኑሮውን በባህርዳር አድርጎ የነበረው ኤልአጅሚ የተባለ ሱዳናዊ እንደገለጸለት ዘገባው አስታውቋል።
በባህርዳር እና በጎንደር ይኖሩ የነበሩ ሱዳናውያን በከተሞቹ ተከስቶ በነበረው ቀውስ ሳቢያ ከፍተኛ ችግር እና መከራ ማሳለፋቸውን ሱዳናዊው ባክሪ አልአጅሚ እንደገለጸለት ያስነበበው ድረገጹ ለሳምንት ያክል መንገዶች መዘጋታቸው፣ ምግብ ቤቶች እና ሲቆች አለመከፈታቸው የመከራ ቀናት እንድናሳልፍ አድርጎናል ማለቱንም አካቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት የመኖሪያ ቪዛቸውን ለማደስ በየወሩ 80 ዶላር እንድንከፍል ያስገድደናል ሲሉ ከችግር ላይ ችግር በማስተናገድ ላይ ነን ሲል ሱዳናዊው ባካሪ መናገሩን ያስነበበው ድረገጹ በክልሉ ቀውስ ከመከሰቱ በፊት የቪዛ ማደሻ ክፍያውን እንዲያስቀርላቸው ለክልሉ መንግስት ጠይቀው እንደነበር መግለጹን አስታውቋል።
ሱዳናውያኑ የኢትዮጵያን ድነበር አቋርጠው ሲገቡ ሁለት አማራጭ እንደሚቀርብላቸው ያመላከተው የድረገጹ ዘገባ ወደ መጠለያ ካምፕ መግባት የሚፈልጉ ሱዳናውያን ምንም አይነት የቪዛም ሆነ ሌላ ክፍያ እንደማይጠየቁ ጠቁሟል። አስ