ዜና፡ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በሱዳን ጉዳይ በሚመክረው የካይሮ ስብሰባ ለመታደም ግብጽ ይገኛሉ፤ ከአልሲሲ ጋር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6/2015 ዓ.ም፡- ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሱዳን ጉዳይ በሚመክረው የካይሮ ስብሰባ ለመታደም ግብጽ ይገኛሉ፤ ትላንት ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ማምሻ ግብጽ የገቡት ዶ/ር አብይ የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በቤተመንግስታቸው አቀባበል እንዳደረጉላቸው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ከአልሲሲ ጋር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ፣ በሁለቱ ሀገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት መምከራቸውም ተገልጿል።

በሱዳን ሰላም ዙሪያ በሚመክረው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የሱዳን አጎራባች ሀገራት መሪዎች ካይሮ መግባታቸውን ያመላከቱት ዘገባዎቹ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ትላንት ጠዋት ላይ ካይሮ መግባታቸውንም አውስተዋል።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና አልሲሲ በይፋ ሲገናኙ ከሶስት አመታት በኋላ መሆኑን የጠቆመው አልአህራም ድረገጽ በሌሎች አለም አቀፍ ስብሰባዎች በተጓዳኝ ተገናኝተው እንደሚያውቁ አውስቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.