እዲስ አበባ፣ታህሳስ 12/ 2015 ዓ.ም ፦ የፌደራል መንግስትና የትግራይ ከፍተኛ የጦር አዛዦች በናይሮቢ ካረን፤ ሞራን ማሰልጠኛ ማእከል፤ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ/ም በፕሪቶርያ ደቡብ እፍሪካ ላይ የተፈራረሙትን የጦርነት ማቆም ስምምነ አፈጻጸምን በተመለከተ በምክክር ላይ እንደሚገኙ አዲስ ስታንዳርድ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
የምክክር መድረኩ በታህሳስ 11 እና 14 ባሉት ጊዜያት ታቅዶ የነበረው ቢሆንም በዛሬው እለት ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ/ም መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል።
እንደ መረጃው ከሆነ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የምክክር መድረክ ሁለቱ ወገኖች ትጥቅ የማስፈታት ሂደት አፈፃፀም ውጤት ሰነድ ላይ የሚወያዩ ሲሆን በተጨማሪም በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ለአፍሪካ ህብረት የክትትል፣ የማረጋገጫ እና ለስምምነቱ ተገዢነት አሰራር የማጣቀሻ ውሎችን ማጠናቀቅ እና ማፅደቅ እንዲሁም ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት ትግበራን በተመለከተ ቀጣይ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በስብሰባው ላይ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የእፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፓናል እባል ኡሁሩ ኬንያታ፣ የኢጋድና የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን ስብሰባው የሚካሄደው በፊዴራል እና በህወሃት ቅሬታ መለዋወጣቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የክትትል እና የማረጋገጫ ቡድን በአስቸኳይ አንዲሰባሰብ ጥሪ እየቀረበበት ባለበት ወቅት ነው፡፡
ቅዳሜ ታህሳስ 8 ቀን 2015ዓ/ም የፌደራል መንግስት ዋና ከተማዋን መቐለ ጨምሮ የመከላክያ አባላት ባልተቆጣጠራቸው ቦታዎች ላይ “የተደራጁ ወንጀሎች” አንዲሁም “ዝርፍያ” በመብዛታቸው መንግስት በትግራይ የሚገኙ ንጹሃን ዜጎች ደህንነት ለመጠበቅ “አስፈላጊውን እርምጃ’ እንደሚወስድ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። መንግስት ወንጀሎኞችን በህግ እንደሚጠይቅም በመግለጫው እክሎ ገልጧል ።
የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው ታህሳስ 9 ቀን 2015ዓ/ም በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ጊዜ ጀምሮ በእነሱ በኩል ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ገልፀው የኢትዮጵያ መንግስት ግን ስምምነቱን በበቂ ሁኔታ እየተገበረ አይደለም ብለዋል፡፡
ዶ/ር ደብረጽዮን ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ መደረግ አለበት፤ የሰብአዊ ድጋፉ መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ብዙ ይቀረዋል፤ ምንም አይነት ገደብ ሊደረግበት አይገባም ሲሉ ፌደራል መንግስትን ወቅሰዋል።
“የኤርትራና የእማራ ታጣቆዎች በሚገኙባቸው የትግራይ አካባቢዎችን ጨምሮ የፌደራል መንግስት እርዳታ በሚያሰራጭባቸው ቦታዎች ማህበረሰቡ በቂ የሰብአዊ ድጋፍ አያገኘ አይደለም፣ በከተማ ያለው ማህበረሰብ ብቻ ነው እርዳተው እያገኘ ያለው በገጠር የሚገኘው ማህበረስብ ክፍል ግን እርዳታ እየደረስው አይደለም” ብለዋል ዶ/ር ደብረጽዮን።
የኤርትራና የአማራ ሃይሎች በሚገኙባቸው ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ጥሰትና ግድያ ወንጀሎች በትግራይ ንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ እንዳለ ብዙ ሪፖርቶች እወጡ ይገኛሉ።
ህዳር 3 ቀን በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት በፕሪቶርያ የተደረሰው ስምምነት መሰረት “የትግራይ ሃይሎች ትጥቅ የማስፈታት ተግባር ተፈጻሚ የሚያደርገው በአንቀጽ 2.1/D ስር “የከባድ መሳርያ ትጥቅ ማስረከብ የውጭ ሃይሎችና ከኢትዮጵያ መከላክያ ውጭ የሆኑት ታጣቂዎች ከክልሉ ሲወጡ እንደሆነ” ተገልጿል።
ህዳር 26 ቀን 2015 ዓም የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ በበኩሉ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት 65 በመቶ የሚጠጋ የትግራይ ክልል ታጣቂ ሃይል ከጦር ግንባር ስፍራዎች ለቆ ወደ ተመደበበት ቦታ መስፈሩን መናገራቸው ይታወሳል ሁኖም የአፍሪካ ህብረት የክትትልና ማረጋገጫ ቡድን በቦታው ባለመገጘቱ ጉዳዩ በተናጠል ሊረጋገጥ አልቻለም።
የዛሬው የናይሮቢ ስብሰባ ውጤት ለሰላም ሂደቱ መተግበር ወሳኝ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። እስ