አዲስ አበባ፣ ህዳር 14/ 2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ በረራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አስታወቁ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት አየር መንገዱ ለዳግም በረራ መዘጋጀቱ በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ለማሳለጥ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው እንደገለፁት በረራው ለመጀመር የታቀደው “በመንግስትና በትግራይ አመራሮች መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎመሆኑን ገልጸዋል።
አየር መንገዱ የአገር ውስጥ በረራ ከሚያደርግባቸው በርካታ መዳረሻዎች መካከል የትግራይ ክልል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው አየር መንገዱ ሲሰጣቸው የነበሩ መደበኛ አገልግሎቶችን ከመስጠት ባለፈ የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ለማፋጠን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል። አስ