እዲስ አበባ ህዳር 28/2015 ዓ.ም፦ ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከአንድ አመት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባት የነበረው የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ዳግም ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር መገናኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ” መቐለ በዚህ ሰዓት ከብሄራዊ ቋት ኃይል እየቀረበላት ነው”፡፡ ከተማዋ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር ዳግም መገናኘቷ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሄደውና የሚመጣውን ኃይል ለመቆጣጠር ያስችለዋል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አንደተናገሩት “ከትላንትናው ዕለተ ማክሰኞ ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በሁሉም ቦታ አለ ብለዋል”፡፡ በዚህ አመት ጥቅምት ወር ላይ ቢቢሲ የሳተላይት ምስሎችን ለማህበራዊ ሚድያ ያጋራ ሲሆን በዚህ የሳተላይት ምስልም መቐለ በዚህ ሁለት አመታት “ከናሳ ሳተላይት ምስል መጥፋትዋን” ያሳያል።
የተከዘ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጪያ ግድብ ከብሄራዊ ኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ውጭ ያለው ውስን የኃይል ተደራሽነት እና ጥቅምት 2013 ዓ.ም አስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም የፌደራል መንግስት የግዚያዊ አስተዳደር ከነበረበት ጊዜ በስተቀር፤ በአብዛኛው ትግራይ ክልል በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል ለሁለት አመት በዘለቀው ጦርነት ምክንያት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ ቆይቷል።
የፌደራል መንግሰት የትግራይ ኃይሎች ሆነ ብሎ የኤሌክትሪክ መሰረታዊ ልማቶች አያወደመ ነው ብሎ የከሰሰ ሲሆን የትግራይ ባለስልጣናትም በበኩላቸው መንግስት ሆነ ብሎ በአስተዳድሩ ስር ባሉ አካባቢዎች የመብራት፣ የባንክ እና የኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን አቋርጧል ብሎ መክሰሳቸው ይታወቃል።
በፌደራል መንግስትና በትግራይ አመራሮች መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው ስምምነት የፌደራል መንግስት የመሰረታዊ ግልጋሎቶች ወደ ነበረበት አንደሚመልስ መስማማቱ ይታወቃል።
አቶ ሞገስ አንዳሉት ከሆነ የመቐለ መስመር ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር የተገናኘው ከአላማጣ ፤ ሞኾኒ በተዘረጋው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ከተደረገለት በኃላ ነው።
ለሽረ ኃይል የሚሰጠው ከተከዘ እስከ አክሱም በተዘረጋው መስመር ስምንት ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማጋጠሙ ጥገናው ወደ ተከዘ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ መቃጠሉን ገልፀው ከሁመራ እስከ ሽረ ድረስ የተዘረጋው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና እንዳተጠናቀቀ አክለው ገልጸዋል። አስ