አዲስ አበባ፣ ህዳር፣ 23/2015 ዓ.ም፡– የትግራይ ወታደራዊ አዛዦች በሁለቱ ተዋጊ ሃይሎች በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ባለስልጣናት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የትግራይ ሃይሎች ከተለያዩ ግንባሮች መውጣት መጀመራቸውን አሳወቁ።
እንደ አዛዦቹ ገለጻ ድርጊቱ የግጭት አፈታት ተግባራትን ለማከናወን ከሚደረገው ጥረት አንዱ አካል ነው። በዚሁ መሰረት የትግራይ ሃይል ከማይቕነጣል፣ ዛላምበሳ፣ ነበለት፣ ጨርጨር፣ ኩኩፍቶ፣ ህጉምቢርዳ፣ በሪ ተክላይ እና አበርገሌ ግንባሮችን ለቅቆ መውጣቱን በህወሃት የፌስቡክ ገፅ የወጣው መግለጫ አመልክቷል።
የናይሮቢ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ የትግራይ ጦር አዛዦች ወደ ቦታቸው በመመለስ አመራሩና መላው የሰራዊቱ አባላት ከግጭት አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ መመሪያ መስጠታቸዉም ተነግሯል።
ይህ የሆነዉ የፎዴራሉ መንግስት የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ መሆኑን ማሰወቁን ተከትሎ ነዉ።
የትግራይ ክልል መሪ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ከሚገኙ የሀይማኖት አባቶች፣ ሲቪክ ማህበራት እና ድርጅቶች ጋር አርብ በሰላም ስምምነት አፈፃፀም ላይ በተደረገ ውይይት ላይ የሰላም ስምምነቱ ለህዝቡ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዉ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የሰላም ስምምነቱን ለማስፈጸም አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ ማሳሰባቸውን ድምፂ ወያኔ ዘግቧል።
በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ውጤት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለዘለቄታው የጦርነት ማቆም ስምምነት (COHA) ተግባራዊ እንዲሆን ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
ዋና ጸሃፊው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በሀገራዊ፣ ክልላዊ እና አለምአቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ሲወያዩ የመንግስታቱ ድርጅት አጠቃላይ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትን ለማሰባሰብ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። አስ