ዜና፡- ዘጠኝ ሪፐብሊካን እና ዴሞክራት ሴናተሮች በኢትዮጵያ ጦርነቱ እንዲቆም፣ የኤርትራ ኃይሎች እንዲወጡ እና ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን ያልተገደበ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲቀርብ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድን ጠየቁ

የአሜሪካ የላይኛው ምክር ቤት

ዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15/2015 ዓ.ም፡- በአፍሪካ ህብረት መሪነት በፌዴራል መንግስት ተወካዮች እና በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መካከል በደቡብ አፍሪካ በሚካሔደው የሰላም ደርድር በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ጦርነት እንዲቆም ከሁለቱ ተቀናቃኝ የአሜሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች (ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን) የተዉጣጡ ዘጠኝ ሴናታሮች (የአሜሪካ የላይኛው ምክር ቤት አባላት) ለጠቅላይ ሚነስትር አብይ አህመድ  በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡ ደብዳቤው ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የኤርትራ ሃይሎች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ እና ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን ያልተገደበ የሰብዓዊ አገልግሎት እንዲሰጥ አሳስቧል፡፡

ቡድኑ በደብዳቤው “በጦርነቱ ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን በሙሉ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ከሰሜን ኢትዮጵያ መውጣትን ጨምሮ ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በድርድሩ የተሳካ ውጤት እንዲመጣ ያልተገደበ ሰብአዊ አገልግሎት ወደ ቀጣናው እንዲደርሱ አጥብቀን እናሳስባለን” ብሏል።  

አፍሪካ ህብረት መራሹ የሰላም ንግግር የፌዴራል መንግስት እና ከትግራይ ክልል ባለስልጣናት የየራሳቸውን የልዑካን ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ መላካቸውን ተከትሎ ነው ጥቅምት 14 እንዲካሄድ ቀጠሮ የተያዘው፡፡

ደብዳቤው መንግስት በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ ያሳየውን ውሳኔ እንደሚደግፈው “ድርድሩ ግጭትን ለማቆም ያለውን ዝግጁነት እንደሚያሳይ” ተስፋ አለው ብሏል።

“ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የተባባሰዉ ጦርነት በሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት እና በጦርነቱ ውስጥ የመጨረሻው አሳዛኝ ምዕራፍ ነው። ግጭቱ ከጀመረበት  ህዳር 2013 ጀምሮ ወደ 2.5 ሚሊዮን የሚገመቱ ንፁሀን ዜጎች ተፈናቅለዋል ፣ ወደ 500ሺ የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል” ብሏል:: አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.