ዜና፡ ኢትዮጵያ በሱዳን ጉዳይ ገለልተኛ አቋም እንዳላት እና ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደምትሻ ጠ/ሚኒስትር አብይ እንዳረጋገጡላት አሜሪካ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9/2015 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ በሱዳን ተፈላሚ ሀይሎች ጉዳይ ገለልተኛ አቋም እንዳላት እና ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደምትሻ ጠ/ሚኒስትር አብይ እንዳረጋገጡላት አሜሪካ አስታወቀች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ይፋ ያደረገው መግለጫ እንደሚያመላክተው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይህን የተናገሩት የመስሪያ ቤቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ሞሊ ፊ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ነው።

ሞሊ ፊ በአዲስ አበባ ከግንቦት 6 እስከ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በነበራቸው ቆይታ ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መምከራቸውን ያስታወቀው መግለጫው ኢትዮጵያ በሱዳን የተፈጠረው ቀውስ በሰላማዊ መንገስ መፍትሔ እልባት እንዲያገኝ እንደምትሻ እና በሁለቱ ተፋላሚወች ምንም አይነት ወገንተኝነት ሳይኖራት ገለልተኛ ናት ማለታቸውን አስታውቋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከኢጋድ፣ የተባበሩት መንግስታት ተወካዮች እና ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን መግለጫው አመላክቷል። ዋነኛ አጀንዳቸውም በሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የአፍሪካ ሀገራት ብሎም የቀጠናው መንግስታት በጋራ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ መሆኑን አስታውቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.