ዜና፡ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ወደ ትግተራይ እንዳይጓዙ በኢትዮጵያ መንግስት መከልከላቸውን ሾልኮ የወጣ መረጃ አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11/2015 ዓ.ም፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ሃላፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአሜሪካ ተቋማት ስለላ እንደተፈጸመባቸው ሾልኮ የወጣ መረጃ ማመላከቱን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ በዘገባው አስታውቋል። ጋዜጣው ተመልክቸዋለሁ ያለው ሾልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው ጉተሬዝ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ወደ ትግራይ በመጓዝ ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ እንደተደረገባቸው እና በዚህም እጅግ መበሳጨታቸውን ለመንግስታቱ ድርጅት ሀላፊዎች መግለጻቸውን ነው።

ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈጸመ በኋላ መሆኑም ተመላክቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ሃላፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጉብኝቱን የተከለከሉት በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ደብዳቤ መሆኑን ያስታወቀው ዘገባው በተመድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን አቅጸስላሴ አምዴን ጠርተው በጉዳዩ ዙሪያ ማናገር ፈልገው እንደነበርም ጠቁሟል።

ጉተሬዝ ሁኔታውን አስመልክተው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊዎች እና ለተለያዩ ሀገራት መሪዎች በብስጭት ማውራታቸውን ያስታወቀው ዘገባው “በስራ ዘመኔ እንዲህ አይነት ደብዳቤ ተጽፎልኝ አያውቅም፣ የመጀመሪያው ደብዳቤ ነው፣ ላረጋግጥ የምፈልገው የመጨረሻውም ይሆናል፤ ደመቀም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሌላ ደብዳቤ የመጻፍ እድል አይኖረውም” ሲሉ መናገራቸውንም አክሎ አካቷል።

ዋና ጸሐፊው ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በኋላ ወደ ኒውዮርክ እንደተመለሱ ለመንግስታቱ ድርጅት ሃላፊዎች እንደተናገሩት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በጉዳዩ ዙሪያ ይቅርታ እንደጠየቋቸው የጋዜጣው ዘገባ ገልጧል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.