አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14/ 2015 ዓ.ም፡- ከትግራይ ክልል የተውጣጡ ልዑክ ቡድን አባላት በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሔደው ድርድር ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ለመደራደር ትናንትና ማታ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል፡፡ በተመሳሳይ የፈዴራል መንግስት ዛሬ ከረፋዱ ባወጣዉ መግለጫ በድርድሩ ላይ እንደሚሳተፍ አረጋግጦ ተደራዳሪ ልዑክ ቡድን ሰኞ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናቱን አሳዉቋል ፡፡
የፌዴራሉ መንግስት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያወጣው መግለጫ እንደሚለዉ “የኢትዮዽያ መንግስት የሰላም ንግግሩ ግጭቱን በሰላም ለመፍታት እና በመከላከያ ሀይል መሥዋዕትነት በመሬት ላይ እየታየ ያለዉን መሻሻል ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው፡፡” ነገር ግን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በፌደራሉ መንግስት በኩል ስልተወከሉ ተደራዳሪዎች ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ ሆኖም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እና ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ ግለሰብ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት የልዑካን ቡድኑ አስር አባላትን ያቀፈ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞትዮስ(ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ምክትል ርሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር(ዶ/ር) እና የብልፅግና ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፅ/ቤት አስተባባሪ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር እንደሚገኙበት የተገለፀ ሲሆን አዲስ ሰታንዳርድ ይህን መረጃ ከመንግሰት ባለስልጣን ማረጋገጥ አልቻልም፡፡
ድርድሩን በማስመልከት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ትናንትና በተነጋገሩበት ወቅት “በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ በቀጠናው ሰላምና ደህንነት ላይ ያለውን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል”፡፡ በተጨማሪም ከደቡብ አፍሪካ አለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስተር ናለዲ ፓንዶር ጋር የኢትዮጵያን የሰላም ደርድር እንዴት ስኬታማ ማድረግ እንደሚቻል ተወያይተውም ነበር፡፡
የትግራይ ተደራዳሪ ልዑክ ቡድን ደቡብ አፍሪካ መድረሱን ትናንት ምሽት የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የውጭ ጉዳይ ፅ/ቤት አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይዎት አረጋግጠዋል፡፡ በአፍሪካ ህብረት መሪነት በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው ድርድር ለመሳተፍ የትግራይ መንግስት ልዑካን ደቡብ አፍሪካ መግባታቸውን ገልፀው ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግ፣ የኤርትራ የይሎች እንዲወጡ እና ወታደራዊ አማራጭ መፍትሔ ሊኖር እንደማይችል ፕሮፌሰር ክንድያ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ፕሮፌሰር ክንደያ ወደ ድርድሩ ማን አንደሚሄድ በውል ባይናገሩም መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አቶ ጌታቸው ረዳና ሌተናል ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ውይይቱን ከሚያደርጉት ቡድን አባላት መካከል ናቸው።
ኔ 27፣ 2014 ዓ.ም. የሰልም ድርድር ቡድኑ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደሚመራ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞትዮስ(ዶ/ር)፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክትር ተማስገን ጥሩነህ፣ የመከላከያ ሰራዊት የመረጃ ደህንነት ሃላፊ ሌ/ ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር(ዶ/ር) እና የብልፅግና ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፅ/ቤት አስተባባሪ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የተካተቱበት ሲሆን አቶ ደመቀ መኮንን በድርድር ሂደቱ ስለመሳተፋቸው የሚጠቁም መረጃ የለም፡፡
የትግራይ ክልላዊ መንግስት ነሓሴ 26 ከሰየማቸው ሰዎች መካከል የትግራይ መንግሰት ፕሬዝዳንት አማካሪ ኣቶ ጌታቸው ረዳ፣ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ደብረጽዮን ገ/ምካኤል (ዾ/ር)፣የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሃላፊ ሌተናል ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ እና የተወሰኑ ከትግራይ ኃይሎች አባላት ጨምሮ ወደ ድርድሩ እንደሚያመሩ አስታውቋል።
የተኩስ አቁም ጥሪዎች እየተበራከቱ ባለበት ወቅት የሰላም ንግግር
የአፍሪካ ህብረት ለሁለተኛ ጊዜ ጥሪ በማደረግ በዛሬው እለት እየተካሄደ ያለው የሰላም ንግግር በአለም አቀፍ ደረጃ በኤርትራ ጦር የሚደገፉ የፌደራል ሃይሎች እና በአማራ ክልል ታጣቂዎች እና በትግራይ ሃይሎች መካከል ያለው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም እና እንዲወጣ ጥሪ እያቀረቡ ባለበት ወቅት ነው። ከትግራይ የተውጣጡ የኤርትራ ሃይሎች የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን እየፈፀሙ እንደሚገኙ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች አመልክተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በዕለተ አርብ ባደረገው ዝግ ስብሰባ በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት ከተወያየ በኋላ መግለጫ ሳይሰጥ ቀርቷል። ” የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት “አፋጣኝ፣ ሁሉን አቀፍ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እና የሰብአዊ አገልግሎት እንደገና እንዲጀመር” የጠየቀ ሲሆን ነገር ግን የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የሆኑት ጋቦን ፣ ጋና እና ኬንያ ምክር ቤቱ በዝግ እንዲመክር የይቀው ቢደረግም ሰለጉዳዩን ግን ምክር ቤቱ መግለጫ ሳይሰጥ ቀርቷል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በትግራይ ክልል “አስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እና የሰብአዊ አገልግሎት እንደገና እንዲጀመር” ጥሪ ካቀረቡ ቡኃላ የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት እና የአውሮፓ ህብረት ጸጥታ ምክርቤት ተገናኝተዋል።
በተናጥል ሀገራት እና የተባበሩተ መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሀገራትም ተመሳሳይ ጥሪዎች ተስተጋብተዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ተወካይ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ እንዳለችው “ሁሉም ወገኖች መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ሰላም የሚመለሱበት ያለፈው ጊዜ ነበር። ጦርነቱ የሚቆምበት እና ለተቸገሩት ሰብአዊ ድጋፍ የሚደረግበት ያለፈው ጊዜ ነበር። የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የጋራ ወታደራዊ ጥቃትን የሚያቆምበት እና ኢትዮጵያ ኤርትራ ወታደሮቿን ከሰሜን ኢትዮጵያ እንድታስወጣ የምትጠይቅበት ያለፈው ጊዜ ነበር”።
በተጨማሪም ባለፉት ሁለት ዓመታት በተካሄደው ጦርነት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን ጠቅሰው አሜሪካ ሊፈጸሙ የሚችሉ ተጨማሪ የጅምላ ግድያ አሳስቧታል” ስትል ተናግራለች፡፡ አክላም አሜሪካ የመፍትሄ አፈታትን በሚያደናቅፉ ሰዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን እና ግጭት እና የሰብአዊ መብት ረገጣ የፈጸሙትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል ብለዋል።
ምንም እንኳን በጥቅምት 20 የፌደራል መንግስት የሰላም ድርድር ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆኑን ቢገልጽም ጥቅምት 17 ቀን ባወጣው መግለጫ “የህወሓትን ተደጋጋሚ ጥቃት እና የውጭ ሃይሎች ጋር የሚያደርገውን ትብብር” ለመከላከል የሚወስደውን እርምጃ” እንደሚቀጥል በመግለፅ የተኩስ አቁም ጥሪን ውድቅ አድርጓል።
የፌደራል መንግስት ” በትግራይ ክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ኤርፖርቶችንና ሌሎች የፌደራል ተቋማትን በአፋጣኝ መቆጣጠር” አስፈላጊ መሆኑን ገልፆ የትግራይ ክልላዊ መንግስትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር፤ ሲቪሎች እና የእርዳታ ሰራተኞች የትግራይ ሃይሎች ከሚጠቀሙባቸው ወታደራዊ መሳሪያዎች እንዲርቁ አሳስቧል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኤርትራ ጦር እና በአማራ ታጣቂዎች የሚደገፈው የፌደራል መንግስት ሽሬ፣ አላማጣ እና ኮረም ተቆጣጥሯል። እስከአሁን ይፋዊ መግለጫ ባይሰጥም የመንግስት ሚዲያዎች እና ጦማሪዎች እንደተናገሩት ጥምር ጦሩ አክሱም እና አድዋ ከተሞችን በመቆጣጠር ላይ ናቸው። አስ