አዲስ አበባ፣ ህዳር 26/2015 ዓ.ም፡- የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት 65 በመቶ የሚጠጋ የትግራይ ክልል ታጣቂ ሃይል ከጦር ግንባር ስፍራዎች ለቆ ወደ ተመደበበት ቦታ መስፈሩን ተናገሩ።
ዋና አዛዡ ትናንት ለክልሉ ሚዲያዎች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ከ60-65 በመቶ የሚሆነውን የትግራይ ሃይልን ከሁሉም የጦር ግንባሮች በማሰባሰብ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ መዘዋወሩን አስታውቀዋል።
ምንም እንኳን የኤርትራ ጦር የአማራ ልዩ ሃይል እና ታጣቂዎች በትግራይ በመኖራቸው የጸጥታ ችግር ቢኖርም የትግራይ ሃይሎችን ከጦርነት ግንባር የመሳብ ተግባር ሰላም ስምምነቱ መሰረት እየተተገበሩ ቆይቷል።
በእኛ በኩል በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት መፈፀም ያለበትን ሁሉ እየተፈፀመ ነው ያሉት ኮማንደሩ ከኤርትራ ሰራዊትና ከአማራ ታጣቂ ሃይሎች ጋር ተያይዞ ያለው ጉዳይ የመከላከያ ሰራዊቱ ሃላፊነት መሆኑ በስምምነቱ በግልፅ መቀመጡን ተናግረዋል።
“የትግራይ ሃይሎች ከጦርነቱ ቀጣና የመውጣት ስራ የሰራዊቱን ሞራል እና ስነ-ልቦና በማይጎዳ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን የተናገሩት ዋና አዝዡ በቅርቡም መቶ በመቶ ጠቅልሎ እንደሚወጣና ወደ ተዘጋጀለት ስፍራ እንደሚያርፍ አስታውቀዋል።
እንደ ዋና አዛዡ ገለጻ፣ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም መከታተልና ያለበት ቡድን እስካሁን ወደ ክልሉ ባይመጣም፣ በትግራይ በኩል ግን በሰላሙ የሰፈረውን ስምምነት ሙሉ በሙሉእየተሰራ ነው።
በትግራይ በኩል በስምምነቱ መሰረት ማድረግ ያለብንን ተግባራዊ እያደረግን ነው ያሉት አዛዡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትም ህገመንግስቱ በሚፈቅድለት መሰረት የክልሉን ፀጥታ ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሆነ እናምናለን ብለዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት እንደተናገረው የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው ተግባር ተስፋ ሰጪ ነው።
“ጦርነቱ በ72 ሰአታት ውስጥ ቆሞ ወደ ትግራይ ለሰብአዊ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ አራት ኮሪደሮች ተከፍተዋል እናም የዕርዳታ ተደራሽነት በየቀኑ እየጨመረ መጥቷል” ብሏል።
ትጥቅ አፈታትን በሚመለከት ባለፈው ሳምንት በሽሬ ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጡ ተወካዮች በአፍሪካ ህብረት በመታገዝ ሰላሙን ለማጠናከር የሚያስችሉ የአሰራር ዘዴዎችን እና የጊዜ ሰሌዳዎችን በማዘጋጀት መጀመሩን አስታውቋል።
የስምምነቱ አፈፃፀም የኤርትራ ሃይሎችም ሆኑ ሌሎች የመከላከያ ሰራዊት አባል ያልሆኑ ሃይሎች ከትግራይ ሙሉ በሙሉ መውጣት እንዳለባቸው በስምነቱ የጠቆመው መግለጫው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂነትን ጨምሮ ብዙ ስራዎች እንደሚቀ አስታውቋል።አስ