አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17/ 2015 ዓ.ም፡- በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራው ከፍተኛ የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ልኡክ ዛሬ ማለዳ በትግራይ ክልል ወና ከተማ መቐለ መግባቱን የክልሉ ሚድያ እስታወቁ ።
የልዑካን ቡድኑ በፌዴራል መንግስትና በትግራይ ክልል ባለስልጣናት ላይ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ከፌዴራል መንግስት የተላከ የመጀመሪያው ከፍተኛ ልዑክ መሆኑ ነው።
የልዑክ ቡድኑ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትንም ያካተተ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ገልጿል።
የልዑካን ቡድኑ ቀደም ሲል በሁለቱ ቡድኖች የተደረሰውን ሰላም ስምምነት ላይ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በተያዘላቸው የግዜ ሰሌዳ መሰረት ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል።
ጉብኝቱ ተግባራዊ የሆነው ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ/ም የፌደራል መንግስትና የትግራይ ባለስልጣናት በናይሮቢ ለሁለተኛ ግዜ ተገናኝተው በፕሪቶርያ ጥቅምት 23 ቀን የተፈራረሙትን ዘላቂ ጦርነት የማቆም ስምምነት ለአፍሪካ ህብረት የክትትል ፣ የማረጋገጫ እና ተገዢነት አሰራር የማጣቀሻ ውሎችን (ToRs) ባፀደቁበት ማግስት ነው።
በሁለቱም ወገኖች የተፈረመዉ የአሰራር የማጣቀሻ ውሎችን እንደሚያመላክተው፤ በሁለቱም አካላት በያንዳዳቸው እንድ የጋራ ተወካይ ኮሚቴ እንዲቋቋም ፣የኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ቡድን ፤ የአፍሪካ ኤክስፐርቶች ቡድን የ10 ሰዎችን ያቀፈ የሰላም ድርድሩን የሚቆጣጠር ማለትም የህወሓት ሃይሎችን ትጥቅ ማስፈታት ሂደት ፤ የውጭ ሃይሎችና ከመከላክያ ውጭ ያሉት የታጠቁ ሃይሎች ከትግራይ ማስወጣትና ካለ ገደብ የሰብአዊ እርዳታዎች ድጋፍን ማድረግን ጨምሮ የሰላም ስምምነቱን የሚከታተል ቡድን ተቋቁሟል።
በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ክልላዊ መንግስት መካከል በስምምነቱ አፈፃፀም ላይ አንዳንድ ክፍተቶች መኖራቸው እየተነሳ ቢሆንም ሁለቱም አካላት ለስምምነቱ ተግባራዊነት ያላቸውን ቁርጠኝነት በየፊናቸው እያረጋገጡ ይገኛሉ። አስ